መጽሐፈ ኢያሱ 10
10
1እንዲህም ሆነ፥ የኢየሩሳሌም ንጉሥ አዶኒጼዴቅ ኢያሱ ጋይን እንደ ያዘ ፈጽሞም እንዳጠፋት፥ በኢያሪኮና በንጉሥዋም ያደረገውን እንዲሁ በጋይና በንጉሥዋ እንዳደረገ፥ የገባዖንም ሰዎች ከእስራኤል ጋር ሰላም እንዳደረጉ በመካከላቸውም እንደ ሆኑ በሰማ ጊዜ፥ 2ገባዖን ከመንግሥታት ከተሞች እንደ አንዲቱ ታላቅ ከተማ ስለ ሆነች፥ ከጋይም ስለ በለጠች፥ ሰዎችዋም ሁሉ ኃያላን ስለ ነበሩ፥ እጅግ ፈራ። 3ስለዚህም የኢየሩሳሌም ንጉሥ አዶኒጼዴቅ ወደ ኬብሮን ንጉሥ ወደ ሆሃም፥ ወደ የርሙት ንጉሥም ወደ ጲርአም፥ ወደ ለኪሶ ንጉሥም ወደ ያፊዓ፥ ወደ አዶላም ንጉሥም ወደ ዳቤር ልኮ፦ ወደ እኔ ውጡ፥ 4ከኢያሱና ከእስራኤልም ልጆች ጋር ሰላም አድርገዋልና ገባዖንን ለመምታት አግዙኝ አለ። 5አምስቱም የአሞራውያን ነገሥታት፥ የኢየሩሳሌም ንጉሥ፥ የኬብሮን ንጉሥ፥ የየርሙት ንጉሥ፥ የለኪሶ ንጉሥ፥ የአዶላም ንጉሥ፥ ከሠራዊቶቻቸው ሁሉ ጋር ተሰብስበው ወጡ፥ ከገባዖንም ጋር ሊጋጠሙ ከበቡአት።
6የገባዖንም ሰዎች ኢያሱ ወደ ሰፈረበት ወደ ጌልገላ ልከው፦ ባሪያዎችህን ለመርዳት እጅህን አትመልስ፥ በተራራማው አገር የሚኖሩ የአሞራውያን ነገሥታት ሁሉ ተሰብስበውብናልና ፈጥነህ ወደ እኛ ውጣ አድነንም እርዳንም አሉት። 7ኢያሱም ከእርሱም ጋር የነበሩ ሰልፈኞች ሁሉ ጽኑዓን ኃያላኑም ሁሉ ከጌልገላ ወጡ። 8እግዚአብሔርም ኢያሱን፦ በእጅህ አሳልፌ ሰጥቼአቸዋለሁና አትፍራቸው፥ ከእነርሱም አንድ ሰው የሚቋቋምህ የለም አለው። 9ኢያሱም ከጌልገላ ሌሊቱን ሁሉ ገሥግሦ በድንገት መጣባቸው። 10እግዚአብሔርም በእስራኤል ፊት አስደነገጣቸው፥ በገባዖንም ታላቅ መምታት መታቸው፥ በቤትሖሮንም ዐቀበት በመንገድ አሳደዳቸው፥ እስከ ዓዜቃና እስከ መቄዳ ድረስ መታቸው። 11ከእስራኤልም ልጆች ፊት እየሸሹ በቤትሖሮን ቁልቁለት ሲወርዱ፥ ወደ ዓዜቃ እስኪደርሱ ድረስ እግዚአብሔር ከሰማይ ታላላቅ የበረዶ ድንጋይ አወረደባቸውና ሞቱ፥ የእስራኤል ልጆች በሰይፍ ከገደሉአቸው ይልቅ በበረዶ ድንጋይ የሞቱት በለጡ።
12እግዚአብሔርም በእስራኤል ልጆች እጅ አሞራውያንን አሳልፎ በሰጠ ቀን ኢያሱ እግዚአብሔርን ተናገረ፥ በእስራኤልም ፊት እንዲህ አለ፦ በገባዖን ላይ ፀሐይ ትቁም፥ በኤሎንም ሸለቆ ጨረቃ፥ 13ሕዝቡም ጠላቶቻቸውን እስኪበቀሉ ድረስ ፀሐይ ቆመ፥ ጨረቃም ዘገየ። ይህስ በያሻር መጽሐፍ የተጻፈ አይደለምን? ፀሐይም በሰማይ መካከል ዘገየ፥ አንድ ቀንም ሙሉ ያህል ለመግባት አልቸኰለም። 14እግዚአብሔር ለእስራኤል ይዋጋ ነበረና እግዚአብሔር የሰውን ቃል የሰማበት እንደዚያ ያለ ቀን ከዚያም በፊት ከዚያም በኋላ አልነበረም።
15ኢያሱም ከእርሱ ጋር እስራኤል ሁሉ ወደ ሰፈራቸው ወደ ጌልገላ ተመለሱ።
16እነዚህም አምስት ነገሥታት ሸሽተው በመቄዳ ዋሻ ተሸሸጉ። 17ለኢያሱም፦ አምስቱ ነገሥታት በመቄዳ ዋሻ ተሸሽገው ተገኙ ብለው ነገሩት። 18ኢያሱም እንዲህ አለ፦ ወደ ዋሻው አፍ ታላላቅ ድንጋይ አንከባልላችሁ፥ ይጠብቁአቸው ዘንድ ሰዎችን በዚያ አኑሩ፥ 19እናንተ ግን አትዘግዩ፥ ጠላቶቻችሁንም አባርሩአቸው፥ በኋላም ያሉትን ግደሉ፥ አምላካችሁም እግዚአብሔር በእጃችሁ አሳልፎ ሰጥቶአቸዋልና ወደ ከተሞቻቸው እንዳይገቡ ከልክሉአቸው አለ። 20እስኪጠፉም ድረስ ኢያሱና የእስራኤል ልጆች በታላቅ መምታት መምታታቸውን በፈጸሙ ጊዜ፥ ከእነርሱም ያመለጡት ወደ ተመሸገ ከተማ በገቡ ጊዜ፥ 21ሕዝብ ሁሉ ኢያሱ ወደ ሰፈረበት ወደ መቄዳ በደኅና ተመለሱ፥ በእስራኤል ልጆች ላይ ምላሱን ማንቀሳቀስ የደፈረ ማንም ሰው የለም።
22ኢያሱም፦ የዋሻውን አፍ ክፈቱ፥ እነዚያንም አምስት ነገሥታት ከዋሻው ወደ እኔ አውጡአቸው አለ። 23እንዲህም አደረጉ፥ አምስቱንም ነገሥታት፥ የኢየሩሳሌምን ንጉሥ የኬብሮንንም ንጉሥ የየርሙትንም ንጉሥ የለኪሶንም ንጉሥ የአዶላምንም ንጉሥ፥ ከዋሻው ወደ እርሱ አወጡአቸው። 24እነዚያንም ነገሥታት ወደ ኢያሱ ባወጡአቸው ጊዜ ኢያሱ የእስራኤልን ሰዎች ሁሉ ጠራ፥ ከእርሱም ጋር የሄዱትን የሰልፈኞች አለቆች፦ ቅረቡ፥ በእነዚህም ነገሥታት አንገት ላይ እግራችሁን አኑሩ አላቸው። ቀረቡም በአንገታቸውም ላይ እግራቸውን አኖሩ። 25ኢያሱም፦ እግዚአብሔር በምትወጉአቸው በጠላቶቻችሁ ሁሉ ላይ እንዲሁ ያደርጋልና አትፍሩ፥ አትደንግጡ፥ ጽኑ፥ አይዞአችሁ አላቸው። 26ከዚህም በኋላ መትተው ገደሉአቸው፥ በአምስቱም ዛፎች ላይ ሰቀሉአቸው፥ እስከ ማታም ድረስ በዛፎቹ ተሰቅለው ቈዩ። 27ፀሐይም ልትገባ በቀረበች ጊዜ ኢያሱ አዘዘ፥ ከዛፎችም አወረዱአቸው፥ ተሸሽገውም በነበሩበት ዋሻ ጣሉአቸው፥ እስከ ዛሬም ድረስ በዋሻው አፍ ታላላቅ ድንጋይ ተደርጎአል።
28በዚያም ቀን ኢያሱ መቄዳን ያዛት፥ እርስዋንና ንጉሥዋንም በሰይፍ ስለት መታ፥ በእርስዋም ያሉትን ነፍሳት ሁሉ ፈጽሞ አጠፋቸው፥ ከእነርሱም አንዱን ስንኳ አላስቀረም፥ በኢያሪኮም ንጉሥ እንዳደረገ በመቄዳ ንጉስ አደረገ።
29ኢያሱም ከእርሱም ጋር እስራኤል ሁሉ ከመቄዳ ወደ ልብና አለፉ፥ ልብናንም ወጉ። 30እግዚአብሔርም እርስዋንና ንጉሥዋን በእስራኤል እጅ አሳልፎ ሰጠ፥ እርስዋንም በእርስዋም ያሉትን ነፍሳት ሁሉ በሰይፍ ስለት መታ፥ በእርስዋም አንዱን ስንኳ አላስቀረም፥ በኢያሪኮም ንጉሥ እንዳደረገው በልብና ንጉሥ አደረገ።
31ኢያሱም ከእርሱም ጋር እስራኤል ሁሉ ከልብና ወደ ለኪሶ አለፉ፥ ከበቡአትም፥ ወጉአትም። 32እግዚአብሔርም ለኪሶን በእስራኤል እጅ አሳልፎ ሰጣት፥ በሁለተኛውም ቀን ያዙአት፥ በልብናም እንዳደረጉት ሁሉ፥ እርስዋን በእርስዋም ያሉትን ነፍሳት ሁሉ በሰይፍ ስለት መቱአቸው።
33በዚያን ጊዜም የጌዝር ንጉሥ ሆራም ለኪሶን ለመርዳት ወጣ፥ ኢያሱም አንድ ስንኳ ሳይቀር እርሱንና ሕዝቡን መታ።
34ኢያሱም ከእርሱም ጋር እስራኤል ሁሉ ከለኪሶ ወደ ኦዶላም አለፉ፥ ከበቡአትም፥ ወጉአትም፥ 35በዚያም ቀን ያዙአት፥ በሰይፍም ስለት መቱአት፥ በለኪሶም እንዳደረገው ሁሉ፥ በእርስዋ ያሉትን ነፍሳት ሁሉ በዚያ ቀን ፈጽሞ አጠፋ።
36ኢያሱም ከእርሱም ጋር እስራኤል ሁሉ ከኦዶላም ወደ ኬብሮን ወጡ፥ ወጉአትም፥ ያዙአትም፥ 37እርስዋንም ንጉሥዋንም ከተሞችዋንም ሁሉ በእርስዋም ያሉትን ነፍሳት ሁሉ በሰይፍ ስለት መቱ፥ በኦዶላም እንዳደረገው ሁሉ ማንንም አላስቀረም፥ እርስዋንም በእርስዋም ያሉትን ነፍሳት ሁሉ ፈጽሞ አጠፋ።
38ኢያሱም ከእርሱም ጋር እስራኤል ሁሉ ወደ ዳቤር ተመለሱ፥ ወጉአትም፥ 39እርስዋንም ንጉሥዋንም ከተሞችዋንም ያዙ፥ በሰይፍም ስለት መቱአቸው፥ በእነርሱም ውስጥ ያሉትን ነፍሳት ሁሉ ፈጽመው አጠፉ፥ ማንንም አላስቀረም፥ በኬብሮን፥ ደግሞ በልብናና በንጉሥዋ እንዳደረገው እንዲሁ በዳቤርና በንጉሥዋ አደረገ።
40እንዲሁም ኢያሱ ምድሪቱን ሁሉ ተራራማውን አገር ደቡቡንም ቈላውንም ቁልቁለቱንም ነገሥታቶቻቸውንም ሁሉ መታ፥ ማንንም አላስቀረም፥ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዳዘዘውም ነፍስ ያለበትን ሁሉ ፈጽሞ አጠፋ። 41ኢያሱም ከቃዴስ በርኔ እስከ ጋዛ ድረስ የጎሶምንም ምድር ሁሉ እስከ ገባዖን ድረስ መታ። 42የእስራኤልም አምላክ እግዚአብሔር ለእስራኤል ስለ ተዋጋላቸው ኢያሱ እነዚህን ነገሥታት ሁሉ ምድራቸውንም በአንድ ጊዜ ያዘ። 43ኢያሱም ከእርሱም ጋር እስራኤል ሁሉ ወደ ሰፈሩ ወደ ጌልገላ ተመለሱ።
Currently Selected:
መጽሐፈ ኢያሱ 10: አማ54
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ