መጽሐፈ ኢያሱ 15
15
1ለይሁዳም ልጆች ነገድ በየወገናቸው እስከ ጺን ምድረ በዳ እስከ ደቡብ መጨረሻ እስከ ኤዶምያስ ዳርቻ ድረስ ዕጣ ሆነላቸው። 2በደቡብም በኩል ያለው ድንበራቸው እስከ ጨው ባሕር መጨረሻ ወደ ደቡብ እስከሚያይ እስከ ባሕር ልሳን ነበረ። 3ከዚያም በአቅረቢም ዐቀበት በደቡብ በኩል ወጣ፥ ወደ ጺንም አለፈ፥ በቃዴስ በርኔ ወደ ደቡብ በኩል ወጣ፥ በሐጽሮንም በኩል አለፈ፥ ወደ አዳርም ወጣ፥ 4ወደ ቀርቃ ዞረ፥ ወደ አጽሞንም አለፈ፥ በግብፅም ወንዝ በኩል ወጣ፥ የድንበሩም መውጫ በባሕሩ አጠገብ ነበረ፥ በደቡብ በኩል ያለው ድንበራቸው ይህ ነው። 5በምሥራቅም በኩል ያለው ድንበር እስከ ጨው ባሕር እስከ ዮርዳኖስም መጨረሻ ነበረ። በሰሜንም በኩል ያለው ድንበር በዮርዳኖስ መጨረሻ እስካለው እስከ ባሕሩ ልሳን ድረስ ነበረ፥ 6ከዚያም ድንበሩ ወደ ቤትሖግላ ወጣ፥ በቤትዓረባ በሰሜን በኩል አለፈ፥ ወደ ሮቤልም ልጅ ወደ ቦሀን ድንጋይ ወጣ፥ 7ድንበሩም ከአኮር ሸለቆ ወደ ዳቤር ወጣ፥ በሰሜን በኩል በአዱሚም ዐቀበት ፊት ለፊት፥ በወንዙ በደቡብ በኩል ወዳለችው ወደ ጌልገላ ተመለከተ፥ ድንበሩም ወደ ቤት ሳሚስ ውኃ አለፈ፥ መውጫውም በዓይንሮጌል አጠገብ ነበረ፥ 8ድንበሩም በሄኖም ልጅ ሸለቆ አጠገብ ኢየሩሳሌም ወደምትባለው ወደ ኢያቡሳዊው ወደ ደቡብ ወገን ወጣ፥ ድንበሩም በራፋይም ሸለቆ ዳር በሰሜን በኩል ባለው በሄኖም ሸለቆ ፊት ለፊት በምዕራብ ወገን ወዳለው ተራራ ራስ ላይ ወጣ፥ 9ድንበሩም ከተራራው ራስ ወደ ኔፍቶ ውኃ ምንጭ ደረሰ፥ ወደ ዔፍሮንም ተራራ ከተሞች ወጣ፥ ቂርያትይዓሪም ወደምትባል ወደ በኣላ ደረሰ። 10ድንበሩም ከበኣላ በምዕራብ በኩል ወደ ሴይር ተራራ ዞረ፥ ክሳሎን ወደምትባል ወደ ይዓርም ተራራ ወገን በሰሜን በኩል አለፈ፥ ወደ ቤትሳሚስ ወረደ፥ በተምና በኩልም አለፈ። 11ድንበሩም ወደ አቃሮን ወደ ሰሜን ወገን ወጣ፥ ወደ ሽክሮን ደረሰ፥ ወደ በኣላ ተራራ አለፈ፥ በየብኒኤል በኩልም ወጣ፥ የድንበሩም መውጫ በባሕሩ አጠገብ ነበረ። 12በምዕራብም በኩል ያለው ድንበር እስከ ታላቁ ባሕርና እስከ ዳርቻው ድረስ ነበረ። ለይሁዳ ልጆች በየወገናቸው በዙሪያው ያለ ድንበራቸው ይህ ነው።
13እግዚአብሔርም ኢያሱን እንዳዘዘው ለዮፎኒ ልጅ ለካሌብ በይሁዳ ልጆች መካከል ቂርያትአርባቅ የምትባለውን ከተማ ድርሻ አድርጎ ሰጠው፥ እርስዋም ኬብሮን ናት፥ ይህም አርባቅ የዔናቅ አባት ነበረ። 14ካሌብም ሦስቱን የዔናቅን ልጆች ሴሲንና አኪመንን ተላሚንም ከዚያ አሳደደ። 15ከዚያም በዳቤር ሰዎች ላይ ወጣ፥ የዳቤርም ስም አስቀድሞ ቂርያትሤፍር ትባል ነበረ። 16ካሌብም፦ ቂርያትሤፍርን ለሚመታ ለሚይዛትም ልጄን ዓክሳን አጋባዋለሁ አለ። 17የካሌብ ወንድም የቄኔዝ ልጅ ጎቶንያል ያዛት፥ ልጁንም ዓክሳን አጋባው። 18እርስዋም ወደ እርሱ በመጣች ጊዜ ከአባትዋ እርሻ እንዲለምን መከረችው፥ እርስዋም ከአህያዋ ወረደች፥ 19ካሌብም፦ ምን ፈለግሽ? አላት። እርስዋም፦ በረከትን ስጠኝ፥ በደቡብም በኩል ያለውን ምድር ሰጥተኸኛልና አሁን ደግሞ የውኃውን ምንጭ ስጠኝ አለችው። እርሱም የላይኛውንና የታችኛውን ምንጭ ሰጣት።
20በየወገኖቻቸውም የይሁዳ ልጆች ነገድ ርስት ይህ ነው።
21በደቡብም በኩል በምድራቸው ዳርቻ አጠገብ እስከ ኤዶምያስ ድንበር ያሉት የይሁዳ ልጆች ነገድ ከተሞች እነዚህ ነበሩ፥ 22ቀብሴኤል፥ ዔደር፥ ያጉር፥ ቂና፥ 23ዲሞና፥ ዓድዓዳ፥ ቃዴስ፥ ሐጾር፥ ዪትናን፥ 24-25ዚፍ፥ ጤሌም፥ በዓሎት፥ ሐጾርሐዳታ፥ ሐጾር የምትባለውም ቂርያትሐጾር፥ 26-27አማም፥ ሽማዕ፥ ሞላዳ፥ ሓጸርጋዳ፥ ሐሽሞን፥ 28ቤትጳሌጥ፥ ሐጸርሹዓል፥ ቤርሳቤህ፥ ቢዝዮትያ፥ 29-30በኣላ፥ ዒዪም፥ ዓጼም፥ ኤልቶላድ፥ 31ኪሲል፥ ሔርማ፥ ጺቅላግ፥ ማድማና፥ ሳንሳና፥ 32ልባዎት፥ ሺልሂም፥ ዓይን፥ ሪሞን፥ ሀያዘጠኝ ከተሞችና መንደሮቻቸው።
33-34በቈላው ኤሽታኦል፥ ጾርዓ፥ አሽና፥ ዛኖዋ፥ 35ዓይንገኒም፥ ታጱዋ፥ ዓይናም፥ የርሙት፥ 36ዓዶላም፥ ሰኰት፥ ዓዜቃ፥ ሽዓራይም፥ ዓዲታይም፥ ግዴራ፥ ግዴሮታይም፥ አሥራ አራት ከተሞችና መንደሮቻቸው።
37-38ጽናን፥ ሐዳሻ፥ ሚግዳልጋድ፥ ዲልዓን፥ 39ምጽጳ፥ ዮቅትኤል፥ ለኪሶ፥ ቦጽቃት፥ 40-41ኦዶላም፥ ከቦን፥ ለሕማስ፥ ኪትሊሽ፥ ግዴሮት፥ ቤትዳጎን፥ ናዕማ፥ መቄዳ፥ አሥራ ስድስት ከተሞችና መንደሮቻቸው።
42-43ልብና፥ ዔቴር፥ ዓሻን፥ ይፍታሕ፥ አሽና፥ 44ንጺብ፥ ቅዒላ፥ አክዚብ፥ መሪሳ፥ ዘጠኝ ከተሞችና መንደሮቻቸው።
45አቃሮን ከተመሸጉና ካልተመሸጉ መንደሮችዋ ጋር፥ 46ከአቃሮንም ጀምሮ እስከ ባሕር ድረስ በአዛጦን አጠገብ ያሉት ሁሉ ከመንደሮቻቸው ጋር።
47አዛጦንና የተመሸጉና ያልተመሸጉ መንደሮችዋም፥ ጋዛና የተመሸጉ ያልተመሸጉም መንደሮችዋ፥ እስከ ግብፅ ወንዝና እስከ ታላቁ ባሕር ዳርቻ ድረስ።
48በተራራማው አገር ሳምር፥ የቲር፥ 49ሶኮ፥ ደና፥ ዳቤር የምትባለው ቂርያትሰና፥ 50-51ዓናብ፥ ኤሽትሞዓ፥ ዓኒም፥ ጎሶም፥ ሖሎን፥ ጊሎ፥ አሥራ አንድ ከተሞችና መንደሮቻቸው።
52-53አራብ፥ ዱማ፥ ኤሽዓን፥ ያኒም፥ ቤትታጱዋ፥ 54አፌቃ፥ ሑምጣ፥ ኬብሮን የምትባል ቂርያትአርባቅ፥ ጺዖር፥ ዘጠኝ ከተሞችና መንደሮቻቸው።
55-56ማዖን፥ ቀርሜሎስ፥ ዚፍ፥ ዩጣ፥ ኢይዝራኤል፥ 57ዮቅድዓም፥ ዛኖዋሕ፥ ቃይን፥ ጊብዓ፥ ተምና፥ አሥር ከተሞችና መንደሮቻቸው።
58-59ሐልሑል፥ ቤትጹር፥ ጌዶር፥ ማዕራት፥ ቤትዓኖት፥ ኤልትቆን፥ ስድስት ከተሞችና መንደሮቻቸው።
60ቂርያትይዓሪም የምትባለው ቂርያትበኣል፥ ረባት፥ ሁለት ከተሞችና መንደሮቻቸው።
61በምድረ በዳ ቤትዓረባ፥ ሚዲን፥ ስካካ፥ 62ኒብሻን፥ የጨው ከተማ፥ ዓይንጋዲ፥ ስድስት ከተሞችና መንደሮቻቸው።
63በኢየሩሳሌም የተቀመጡትን ኢያቡሳውያንን ግን የይሁዳ ልጆች ሊያሳድዱአቸው አልተቻላቸውም፥ ኢያቡሳውያንም እስከ ዛሬ በይሁዳ ልጆች መካከል በኢየሩሳሌም ውስጥ ተቀምጠዋል።
Currently Selected:
መጽሐፈ ኢያሱ 15: አማ54
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ