መጽሐፈ ኢያሱ 21
21
1የሌዋውያን አባቶች አለቆች ወደ ካህኑ ወደ አልዓዛር፥ ወደ ነዌም ልጅ ወደ ኢያሱ፥ ወደ እስራኤልም ልጆች ነገዶች አለቆች ቀረቡ፥ 2በከነዓን ምድር ባለችው በሴሎ፦ እግዚአብሔር በሙሴ እጅ የምንቀመጥባቸውን ከተሞች፥ ለከብቶቻችንም መሰምርያዎች ትሰጡን ዘንድ አዝዞአል ብለው ተናገሩአቸው። 3የእስራኤልም ልጆች እንደ እግዚአብሔር ትእዛዝ ከርስታቸው እነዚህን ከተሞችና መሰምርያቸውን ለሌዋውያን ሰጡ።
4ለቀዓትም ወገኖች ዕጣ ወጣ፥ ሌዋውያንም ለነበሩ ለካህኑ ለአሮን ልጆች ከይሁዳ ነገድ፥ ከስምዖንም ነገድ፥ ከብንያምም ነገድ አሥራ ሦስት ከተሞች በዕጣ ሆኑላቸው።
5ለቀሩትም ለቀዓት ልጆች ከኤፍሬም ነገድ፥ ከዳንም ነገድ፥ ከምናሴም ነገድ እኩሌታ አሥር ከተሞች በዕጣ ሆኑላቸው።
6ለጌድሶንም ልጆች ከይሳኮር ነገድ፥ ከአሴርም ነገድ፥ ከንፍታሌምም ነገድ፥ በባሳንም ካለው ከምናሴ ነገድ እኩሌታ አሥራ ሦስት ከተሞች በዕጣ ሆኑላቸው።
7ለሜራሪም ልጆች በየወገኖቻቸው ከሮቤል ነገድ፥ ከጋድም ነገድ፥ ከዛብሎንም ነገድ አሥራ ሁለት ከተሞች ሆኑላቸው።
8እግዚአብሔርም በሙሴ እጅ እንዳዘዘ የእስራኤል ልጆች እነዚህን ከተሞችና መሰምርያቸውን ለሌዋውያን በዕጣ ሰጡ። 9ከይሁዳም ልጆች ነገድ ከስምዖንም ልጆች ነገድ በስማቸው የተጠሩትን እነዚህን ከተሞች ሰጡ። 10የፊተኛው ዕጣ ለእነርሱ ስለ ወጣ የሌዊ ልጆች የቀዓት ወገን ለሆኑ ለአሮን ልጆች ሆኑ። 11በይሁዳ ተራራማ አገር ያለችውን ቂርያትአርባቅ የምትባለውን ከተማ በዙሪያዋም ያለውን መሰምርያ ሰጡአቸው፥ እርስዋም ኬብሮን ናት፥ ይህም አርባቅ የዔናቅ አባት ነበረ። 12የከተማይቱን እርሻ ግን መንደሮችዋንም ለዮፎኔ ልጅ ለካሌብ ርስት አድርገው ሰጡት።
13ለካህኑም ለአሮን ልጆች እነዚህን ሰጡ፥ ለነፍሰ ገዳይ መማፀኛ ከተማ የሆነችውን ኬብሮንና መሰምርያዋን፥ ልብናንና መሰምርያዋን፥ 14የቲርንና መሰምርያዋን፥ ኤሽትሞዓንና መሰምርያዋን፥ 15ሖሎንንና መሰምርያዋን፥ ዳቤርንና መሰምርያዋን፥ 16ዓይንንና መሰምርያዋን፥ ዮጣንና መሰምርያዋን፥ ቤትሳሜስንና መሰምርያዋን፥ ከእነዚህ ከሁለቱ ነገዶች ዘጠኝ ከተሞችን ሰጡ። 17ከብንያምም ነገድ ገባዖንንና መሰምርያዋን፥ ናሲብንና መሰምርያዋን፥ 18አናቶትንና መሰምርያዋን፥ አልሞንና መሰምርያዋን፥ አራት ከተሞችን ሰጡ። 19የአሮን ልጆች የካህናት ከተሞች ከመሰምርያቸው ጋር አሥራ ሦስት ናቸው።
20ለቀሩትም ለቀዓት ልጆች ወገኖች ሌዋውያን የዕጣቸው ከተሞች ከኤፍሬም ነገድ ደረሱአቸው። 21በኤፍሬም ተራራማ አገር ለነፍሰ ገዳይ መማፀኛ ከተማ የሆነችውን ሴኬምንና መሰምርያዋን፥ ጌዝርንና መሰምርያዋን፥ 22ቂብጻይምንና መሰምርያዋን፥ ቤትሖሮንንና መሰምርያዋን፥ አራቱን ከተሞች ሰጡአቸው። 23ከዳንም ነገድ ኤልተቄንና መሰምርያዋን፥ ገባቶንንና መሰምርያዋን፥ ኤሎንንና መሰምርያዋን፥ 24ጋትሪሞንንና መሰምርያዋን፥ አራቱን ከተሞች ሰጡአቸው። 25ከምናሴም ነገድ እኩሌታ ታዕናክንና መሰምርያዋን፥ ጋትሪሞንንና መሰምርያዋን፥ ሁለቱን ከተሞች ሰጡአቸው። 26የቀሩት የቀዓት ልጆች ወገኖች ከተሞች ሁሉ ከመሰምርያቸው ጋር አሥር ናቸው።
27ለሌዋውያንም ወገኖች ለጌድሶን ልጆች ከምናሴ ነገድ እኩሌታ ለነፍሰ ገዳይ መማፀኛ ከተማ በባሳን ውስጥ የሆነቸውን ጎላንንና መሰምርያዋን፥ በኤሽትራንና መሰምርያዋን፥ ሁለቱን ከተሞች ሰጡአቸው። 28ከይሳኮርም ነገድ ቂሶንንና መሰምርያዋን፥ ዳብራትንና መሰምርያዋን፥ 29የርሙትንና መሰምርያዋን፥ ዓይንጋኒምንና መሰምርያዋን፥ አራቱን ከተሞች ሰጡአቸው። 30ከአሴርም ነገድ ሚሽአልንና መሰምርያዋን፥ ዓብዶንንና መሰምርያዋን፥ 31ሔልቃትንና መሰምርያዋን፥ ረአብንና መሰምርያዋን፥ አራቱን ከተሞች ሰጡአቸው። 32ከንፍታሌምም ነገድ ለነፍሰ ገዳይ መማፀኛ ከተማ የሆነቸውን በገሊላ ውስጥ ቃዴስንና መሰምርያዋን፥ ሐሞትዶንና መሰምርያዋን፥ ቀርታንንና መሰምርያዋን፥ ሦስቱን ከተሞች ሰጡአቸው። 33የጌድሶን ልጆች ከተሞች ሁሉ በየወገኖቻቸው አሥራ ሦስት ከተሞች ከመሰምርያቸው ጋር ናቸው።
34ከሌዋውያንም ለቀሩት ለሜራሪ ልጆች ወገን ከዛብሎን ነገድ ዮቅንዓምንና መሰምርያዋን፥ 35ቀርታንና መሰምርያዋን፥ ዲሞናንና መሰምርያዋን፥ ነህላልንና መሰምርያዋን፥ አራቱን ከተሞች ሰጡ። 36ከሮቤልም ነገድ ቦሶርንና መሰምርያዋን፥ ያሀጽንና መሰምርያዋን፥ 37ቅዴሞትንና መሰምርያዋን፥ ሜፍዓትንና መሰምርያዋን፥ አራቱን ከተሞች ሰጡ። 38ከጋድም ነገድ ለነፍሰ ገዳይ መማፀኛ ከተማ የሆነችውን በገለዓድ ውስጥ ራሞትንና መሰምርያዋን፥ መሃናይምንና መሰምርያዋን፥ 39ሐሴቦንንና መሰምርያዋን፥ ኢያዜርንና መሰምርያዋን፥ አራቱን ከተሞች ሰጡ። 40ከሌዋውያን ወገኖች የቀሩት የሜራሪ ልጆች ከተሞች ሁሉ በየወገኖቻቸው እነዚህ ነበሩ፥ ዕጣቸውም አሥራ ሁለት ከተማ ነበረ።
41በእስራኤል ልጆች ርስት መካከል የነበሩት የሌዋውያን ከተሞች ሁሉ አርባ ስምንት ከተሞችና መሰምርያቸው ነበሩ። 42እነዚህም ከተሞች እያንዳንዳቸው ከመሰምርያቸው ጋር ነበሩ፥ እነዚህም ከተሞች ሁሉ እንዲሁ ነበሩ።
43እግዚአብሔርም ይሰጣቸው ዘንድ ለአባቶቻቸው የማለላቸው ምድር ሁሉ ለእስራኤል ሰጠ፥ ወረሱአትም፥ ተቀመጡባትም። 44እግዚአብሔርም ለአባቶቻቸው እንደ ማለላቸው በዙሪያቸው ካሉት አሳረፋቸው፥ ከጠላቶቻቸውም ሁሉ ይቋቋማቸው ዘንድ ማንም ሰው አልቻለም፥ እግዚአብሔርም ጠላቶቻቸውን ሁሉ በእጃቸው አሳልፎ ሰጣቸው። 45እግዚአብሔር ለእስራኤል ቤት ከተናገረው መልካም ነገር ሁሉ ተፈጸመ እንጂ ምንም አልቀረም።
Currently Selected:
መጽሐፈ ኢያሱ 21: አማ54
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ