መኃልየ መኃልይ 3
3
1ሌሊት በምንጣፌ ላይ
ነፍሴ የወደደችውን ፈለግሁት፥
ፈለግሁት አላገኘሁትም።
2እነሣለሁ በከተማይቱም እዞራለሁ፥
ነፍሴ የወደደችውን
በጎዳናና በአደባባይ እፈልጋለሁ፥
ፈለግሁት አላገኘሁትም።
3ከተማይቱን የሚዞሩት ጠባቂዎች አገኙኝ፥
ነፍሴ የወደደችውን አያችሁትን? አልኋቸውም።
4ከእነርሱም ጥቂት እልፍ ብዬ
ነፍሴ የወደደችውን አገኘሁት፥ ያዝሁትም
ወደ እናቴም ቤት ወደ ወላጅ እናቴም እልፍኝ
እስካገባው ድረስ አልተውሁትም።
5እናንተ የኢየሩሳሌም ቈንጃጅት ሆይ፥
እርሱ እስኪፈልግ ድረስ፥
ፍቅርን እንዳታስነሡትና እንዳታነሣሡት
በሚዳቋ በምድረ በዳም ዋላ አምላችኋለሁ።
6መዓዛም እንደ ከርቤና እንደ ዕጣን የሆነችው፥
ከልዩ ከነጋዴ ቅመም ሁሉ የሆነችው፥
ይህች ከምድረ በዳ እንደ ጢስ ምስሶ የወጣችው ማን ናት?
7እነሆ፥ የሰሎሞን አልጋ ናት፥
ከእስራኤል ኃያላን ስድሳ ኃያላን በዙሪያው ናቸው።
8ሁሉም ሰይፍ የያዙ ሰልፈኞች ናቸው፥
በሌሊት ከሚወድቀው ፍርሃት የተነሣ
ሰው ሁሉ ሰይፉ በወገቡ አለ።
9ንጉሡ ሰሎሞን መሸከሚያን
ከሊባኖስ እንጨት ለራሱ አሠራ።
10ምሰሶቹን የብር፥ መደገፊያውንም የወርቅ፥
መቀመጫውንም ሐምራዊ ግምጃ አደረገ፥
ውስጡ በኢየሩሳሌም ቈነጃጅት ፍቅር የተለበጠ ነው።
11እናንተ የጽዮን ቈነጃጅት፥ ውጡ፥
እናቱ በሠርጉ ቀንና በልቡ ደስታ ቀን ያደረገችለትን አክሊል ደፍቶ ንጉሥ ሰሎሞንን እዩ።
Currently Selected:
መኃልየ መኃልይ 3: አማ54
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ