ዘፍጥረት 11
11
የባቤል ግንብ
1በዚያን ጊዜ ሰዎች ሁሉ የሚናገሩትና የሚግባቡበት ቋንቋ አንድ ብቻ ነበር። 2ሰዎቹም ምሥራቁን#11፥2 ወይም ከምሥራቅ፣ በምሥራቅ ይዘው ሲጓዙ፣ በሰናዖር#11፥2 ባቢሎንን ያመላክታል። አንድ ሜዳ አግኝተው በዚያ ሰፈሩ።
3እነርሱም እርስ በርሳቸው፣ “ኑ፤ ጡብ እንሥራ፤ እስኪበቃውም በእሳት እንተኵሰው” ተባባሉ። በድንጋይ ፈንታ ጡብ፣ ለማያያዣም ቅጥራን ተጠቀሙ። 4ከዚያም “ለስማችን መጠሪያ እንዲሆንና በምድር ላይ እንዳንበተን፣ ኑ፤ ከተማ፣ ሰማይ የሚደርስ ግንብም ለራሳችን እንሥራ” አሉ።
5 እግዚአብሔር (ያህዌ) ግን ሰዎቹ ይሠሩ የነበሩትን ከተማና ግንብ ለማየት ወረደ። 6እግዚአብሔርም (ያህዌ) እንዲህ አለ፤ “እንዲህ እንደ አንድ ሕዝብ አንድ ቋንቋ በመናገር ይህን ማድረግ ከጀመሩ፣ ከእንግዲህ ያቀዱትን ሁሉ ማከናወን አያዳግታቸውም። 7ኑ እንውረድ፤ እርስ በርሳቸውም እንዳይግባቡ ቋንቋቸውን እንደበላልቀው።”
8ስለዚህ እግዚአብሔር (ያህዌ) በምድር ሁሉ ላይ በታተናቸው፤ ከተማዋንም መሥራት አቆሙ። 9እግዚአብሔር (ያህዌ) በዚያ የመላውን ዓለም ቋንቋ ስለ ደበላለቀ የከተማዪቱ ስም ባቤል#11፥9 ባቢሎንን ያመላክታል። ባቤል የሚለው ቃል ድንግርታ የሚል ትርጕም ካለው የዕብራይስጥ ቃል ጋር አንድ ዐይነት ድምፅ አለው። ተባለ። ከዚያም እግዚአብሔር (ያህዌ) ሰዎቹን በምድር ሁሉ በተናቸው።
ከሴም እስከ አብራም
11፥10-27 ተጓ ምብ – ዘፍ 10፥21-32፤ 1ዜና 1፥17-27
10የሴም ትውልድ ይህ ነው፦
ሁለት ዓመት ከጥፋት ውሃ በኋላ ሴም በ100 ዓመቱ አርፋክስድን ወለደ። 11ሴም፣ አርፋክስድን ከወለደ በኋላ 500 ዓመት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችን ወለደ።
12አርፋክስድ በ35 ዓመቱ ሳላን ወለደ፤ 13ሳላን ከወለደ በኋላ አርፋክስድ 403 ዓመት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችና ሴቶችን ወለደ።#11፥12-13 ከዕብራይስጡ ጋር ተመሳሳይ ሲሆን፣ ሰብዓ ሊቃናት ግን (በተጨማሪ ሉቃ 3፥35-36 እና የዘፍ 10፥24 ማብ ይመ) እንዲሁ ይሉታል፤ 12 በ35 ዓመት ቃይናንን ወለደ፤ 13 ቃይናንን ከወለደ በኋላ፣ አርፋክስድ 430 ዓመት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችን ወለደ፤ ቃይናንም 130 ዓመት ከኖረ በኋላ ሳላን ወለደ፤ ሳላንን ከወለደ በኋላ፣ ቃይናን 330 ዓመት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችን ወለደ ይላል።
14ሳላ በ30 ዓመቱ ዔቦርን ወለደ፤ 15ዔቦርን ከወለደ በኋላ ሳላ 403 ዓመት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችን ወለደ።
16ዔቦር በ34 ዓመቱ ፋሌቅን ወለደ፤ 17ፋሌቅን ከወለደ በኋላ ዔቦር 430 ዓመት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችን ወለደ።
18ፋሌቅ በ30 ዓመቱ ራግውን ወለደ፤ 19ራግውን ከወለደ በኋላ ፋሌቅ 209 ዓመት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችን ወለደ።
20ራግው በ32 ዓመቱ ሴሮሕን ወለደ፤ 21ሴሮሕን ከወለደ በኋላ ራግው 207 ዓመት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችን ወለደ።
22ሴሮሕ በ30 ዓመቱ ናኮርን ወለደ፤ 23ናኮርን ከወለደ በኋላ ሴሮሕ 200 ዓመት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችን ወለደ።
24ናኮር በ29 ዓመቱ ታራን ወለደ፤ 25ታራን ከወለደ በኋላ ናኮር 119 ዓመት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችን ወለደ።
26ታራ 70 ዓመት ከሆነው በኋላ አብራምን፣ ናኮርንና ሐራንን ወለደ።
27የታራ ትውልድ ይህ ነው፦
ታራ፣ አብራምን ናኮርንና ሐራንን ወለደ፤
ሐራንም ሎጥን ወለደ። 28ሐራን፣ አባቱ ታራ ገና በሕይወት እንዳለ በከለዳውያን ምድር በምትገኘው በተወለደባት ከተማ በዑር ሞተ። 29አብራምና ናኮር ሁለቱም ሚስት አገቡ፤ የአብራም ሚስት ሦራ ስትባል፣ የናኮር ሚስት ደግሞ ሚልካ ትባል ነበር፤ ሚልካም የሐራን ልጅ ናት፤ ሐራንም የሚልካና የዮስካ አባት ነበረ። 30ሦራ መካን ነበረች፤ ልጅ አልነበራትም።
31ታራ ልጁን አብራምን፣ ሐራን የወለደውን የልጅ ልጁን ሎጥን እንዲሁም የአብራምን ሚስት ምራቱን ሦራን ይዞ ወደ ከነዓን ለመሄድ በከለዳውያን ምድር ከምትገኘው ከዑር አብረው ወጡ፤ ነገር ግን ካራን በደረሱ ጊዜ በዚያ ተቀመጡ።
32ታራ 205 ዓመት ኖሮ በካራን ሞተ።
Currently Selected:
ዘፍጥረት 11: NASV
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™
የቅጅ መብት © 2001 በ Biblica, Inc.
ፈቃድ የተገኘባቸው ናቸው። መብቱ በመላው ዓለም በሕግ የተጠበቀ።
Holy Bible, New Amharic Standard Version™ (Addisu Medebegna Tirgum™)
Copyright © 2001 by Biblica, Inc.
Used with permission. All rights reserved worldwide.