1 ዜና መዋዕል 22:19 - Compare All Versions

1 ዜና መዋዕል 22:19 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

አሁ​ንም አም​ላ​ካ​ች​ሁን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትፈ​ልጉ ዘንድ ልባ​ች​ሁ​ንና ነፍ​ሳ​ች​ሁን ስጡ፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስም ወደ​ሚ​ሠ​ራው ቤት የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የቃል ኪዳ​ኑን ታቦ​ትና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ንዋየ ቅድ​ሳት ታመጡ ዘንድ ተነ​ሥ​ታ​ችሁ የአ​ም​ላ​ክን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መቅ​ደስ ሥሩ።”

1 ዜና መዋዕል 22:19 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

አሁንም እግዚአብሔር አምላካችሁን ለመፈለግ ልባችሁንና ነፍሳችሁን ሰብስቡ። የእግዚአብሔርን የኪዳኑን ታቦትና ንዋያተ ቅድሳቱን ለእግዚአብሔር ስም ወደሚሠራው ቤተ መቅደስ እንድታመጡ የእግዚአብሔር አምላክን መቅደስ ሥሩ።”

1 ዜና መዋዕል 22:19 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

አሁንም አምላካችሁን እግዚአብሔርን ትፈልጉ ዘንድ ልባችሁንና ነፍሳችሁን ስጡ፤ ለእግዚአብሔርም ስም ወደሚሠራው ቤት የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳኑን ታቦትና የእግዚአብሔርን ንዋየ ቅድሳት ታመጡ ዘንድ ተነሥታችሁ የአምላክን የእግዚአብሔርን መቅደስ ሥሩ።”

1 ዜና መዋዕል 22:19 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

እንግዲህ አምላካችሁን እግዚአብሔርን በፍጹም ልባችሁና በፍጹም ነፍሳችሁ አገልግሉ፤ የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦትና እግዚአብሔርን ለማምለክ መገልገያ የሆኑትን ንዋያተ ቅድሳት ሁሉ አምጥታችሁ በውስጡ ማኖር ትችሉ ዘንድ ቤተ መቅደሱን ለክብሩ መሥራት ጀምሩ።”

1 ዜና መዋዕል 22:19 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

አሁንም አምላካችሁን ጌታን ለመሻት ልባችሁንና ነፍሳችሁን ለእርሱ አሳልፋችሁ ስጡ፤ ለጌታም ስም ወደሚሠራው ቤት የጌታን የቃል ኪዳኑን ታቦትና የእግዚአብሔርን ንዋየ ቅድሳት ለማምጣት ተነሥታችሁ የጌታን የእግዚአብሔርን መቅደስ ሥሩ።”