1 ዜና መዋዕል 28:20 - Compare All Versions
1 ዜና መዋዕል 28:20 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
ዳዊትም ልጁን ሰሎሞንን፥ “ጠንክር፤ ሰው ሁን፤ አይዞህ፥ አድርገውም፤ አምላኬ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነውና አትፍራ፤ አትደንግጥም፤ ለእግዚአብሔርም ቤት አገልግሎት የሚሆነውን ሥራ ሁሉ እስክትፈጽም ድረስ እርሱ አይተውህም፤ አይጥልህምም። እነሆ፥ የእግዚአብሔር ቤት ሕንጻ ምሳሌ፥ የአደባባዩ፥ የቤተ መዛግብቱ፥ የሰገነቱ፥ የውስጡ ቤተ መዛግብት፥ የስርየት ቤቱና፥ የእግዚአብሔር ቤት ምሳሌ።
1 ዜና መዋዕል 28:20 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
ደግሞም ዳዊት ልጁን ሰሎሞንን እንዲህ አለው፤ “እንግዲህ በርታ፤ ጠንክር፤ ሥራውንም ጀምር። አትፍራ፤ ተስፋም አትቍረጥ፤ እግዚአብሔር አምላኬ ከአንተ ጋራ ነውና፤ እርሱም የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አገልግሎት ሥራ እስኪፈጸም ድረስ አይተውህም፤ አይጥልህም።
1 ዜና መዋዕል 28:20 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))
ዳዊትም ልጁን ሰሎሞንን “ጠንክር! አይዞህ! አድርገውም! አምላኬ እግዚአብሔር አምላክ ከአንተ ጋር ነውና አትፍራ፤ አትደንግጥም፤ ለእግዚአብሔርም ቤት አገልግሎት የሚሆነው ሥራ ሁሉ እስኪፈጸም ድረስ እርሱ አይተውህም፤ አይጥልህምም።
1 ዜና መዋዕል 28:20 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)
ንጉሥ ዳዊት ለልጁ ለሰሎሞንም እንዲህ አለ፤ “አይዞህ በርታ ሥራውንም በቶሎ ጀምር፤ ምንም ነገር አይግታህ፤ እኔ የማገለግለው እግዚአብሔር አምላክ ከአንተ ጋር ነው፤ ለቤተ መቅደሱ ሥራ ያለህን አገልግሎት እስክትፈጽም ድረስ ከአንተ አይለይም፤ አይተውህም፤ ከቶም አይጥልህም፤
1 ዜና መዋዕል 28:20 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))
ዳዊትም ልጁን ሰሎሞንን እንዲህ አለው፦ “ጠንክር፥ አይዞህ፥ አድርገውም፤ አምላኬ እግዚአብሔር አምላክ ከአንተ ጋር ነውና አትፍራ፥ አትደንግጥም፥ ለእግዚአብሔርም ቤት አገልግሎት የሚሆነው ሥራ ሁሉ እስኪፈጸም ድረስ እርሱ አይተውህም፥ አይጥልህምም።