1 ዜና መዋዕል 4:10 - Compare All Versions

1 ዜና መዋዕል 4:10 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

ያግ​ቤ​ጽም፥ “እባ​ክህ፥ መባ​ረ​ክን ባር​ከኝ፥ ሀገ​ሬ​ንም አስ​ፋው፤ እጅ​ህም ከእኔ ጋር ትሁን፤ እን​ዳ​ያ​ሳ​ዝ​ነ​ኝም ምል​ክት አድ​ር​ግ​ልኝ” ብሎ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን አም​ላክ ጠራ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የለ​መ​ነ​ውን ሰጠው።

1 ዜና መዋዕል 4:10 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

ያቤጽም፣ “አቤቱ፤ እንድትባርከኝ፣ ግዛቴንም እንድታሰፋልኝ እለምንሃለሁ፤ እጅህ ከእኔ ጋራ ትሁን፤ ከሥቃይና ከጕዳትም ጠብቀኝ” በማለት ወደ እስራኤል አምላክ ጮኸ። እግዚአብሔርም የለመነውን ሰጠው።

1 ዜና መዋዕል 4:10 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

ያቤጽም “እባክህ! መባረክን ባርከኝ፤ አገሬንም አስፋው፤ እጅህም ከእኔ ጋር ትሁን፤ እንዳያሳዝነኝም ከክፋት ጠብቀኝ፤” ብሎ የእስራኤልን አምላክ ጠራ፤ እግዚአብሔርም የለመነውን ሰጠው።

1 ዜና መዋዕል 4:10 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

ያዕቤጽም “አምላኬ ሆይ፥ ባርከኝ፤ ሰፊ ምድርንም ስጠኝ፤ እጅህ ከእኔ ጋር ይሁን፤ ሥቃይ ሊያስከትልብኝ ከሚችል ከማንኛውም ክፉ ነገር ጠብቀኝ” በማለት ወደ እስራኤል አምላክ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፤ እግዚአብሔርም የለመነውን ሰጠው።

1 ዜና መዋዕል 4:10 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

ያቤጽም፦ “እባክህ፥ መባረክን ባርከኝ፥ አገሬንም አስፋው፤ እጅህም ከእኔ ጋር ይሁን፤ እንዳይጎዳኝም ከክፋት ጠብቀኝ” ብሎ የእስራኤልን አምላክ ጠራ፤ እግዚአብሔርም የለመነውን ሰጠው።