1 ነገሥት 10:24 - ሁሉንም ስሪቶች ያወዳድሩ
1 ነገሥት 10:24 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
ዓለሙ ሁሉ እግዚአብሔር በልቡ ያኖረውን ጥበብ ለመስማት ከሰሎሞን ጋራ መገናኘት ይፈልግ ነበር።
1 ነገሥት 10:24 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)
በመላው ዓለም የሚገኙ ሰዎችም ሁሉ እግዚአብሔር የሰጠውን ጥበብ የሞላበትን ንግግር ይሰሙ ዘንድ ወደ እርሱ መምጣት ይፈልጉ ነበር፤
1 ነገሥት 10:24 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
የምድርም ነገሥት ሁሉ እግዚአብሔር በልቡ ያኖረለትን ጥበቡን ይሰሙ ዘንድ የሰሎሞንን ፊት ለማየት ይሹ ነበር።
1 ነገሥት 10:24 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))
ምድርም ሁሉ እግዚአብሔር በልቡ ያኖረለትን ጥበቡን ይሰማ ዘንድ የሰሎሞንን ፊት ይመኝ ነበር።
1 ነገሥት 10:24 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))
በመላው ዓለም የሚገኙ ሰዎችም ሁሉ እግዚአብሔር የሰጠውን ጥበብ የሞላበትን ንግግር ይሰሙ ዘንድ ወደ እርሱ መምጣት ይፈልጉ ነበር።