1 ነገሥት 17:14 - Compare All Versions

1 ነገሥት 17:14 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላ​ልና፦ በም​ድር ላይ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዝናብ እስ​ከ​ሚ​ሰ​ጥ​በት ቀን ድረስ፥ ዱቄቱ ከማ​ድ​ጋው አይ​ጨ​ረ​ስም፥ ዘይ​ቱም ከማ​ሰ​ሮው አይ​ጐ​ድ​ልም።”

1 ነገሥት 17:14 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘እግዚአብሔር ለምድሪቱ ዝናብ እስከሚሰጥበት ዕለት ድረስ፤ ከማድጋው ዱቄት አይጠፋም፤ ከማሰሮውም ዘይት አያልቅም።’ ”

1 ነገሥት 17:14 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና ‘በምድር ላይ እግዚአብሔር ዝናብ እስከሚሰጥበት ቀን ድረስ፥ ዱቄቱ ከማድጋ አይጨረስም፤ ዘይቱም ከማሰሮው አይጎድልም።’”

1 ነገሥት 17:14 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ‘እኔ እግዚአብሔር ዝናብን እስከማወርድ ድረስ ዱቄቱ ከማኖሪያው ዕቃ፥ ዘይቱም ከማሰሮው ከቶ አያልቅም’ ሲል ተናግሮአል።”

1 ነገሥት 17:14 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

የእስራኤል አምላክ ጌታ እንዲህ ይላልና፦ ‘ጌታ ለምድሪቱ ዝናብ እስከሚሰጥበት ዕለት ድረስ፤ ከማድጋው ዱቄት አይጠፋም፤ ከማሰሮው ዘይት አያልቅም።’”