1 ነገሥት 18:30 - Compare All Versions
1 ነገሥት 18:30 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
ኤልያስም ሕዝቡን ሁሉ፥ “ወደ እኔ ቅረቡ” አላቸው። ሕዝቡም ሁሉ ወደ እርሱ ቀረቡ።
1 ነገሥት 18:30 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
ከዚያም ኤልያስ ሕዝቡን በሙሉ፣ “ወደ እኔ ቅረቡ” አላቸው፤ ሕዝቡም ሁሉ ወደ እርሱ ቀረቡ፤ እርሱም ፈርሶ የነበረውን የእግዚአብሔር መሠዊያ ሠራ።
1 ነገሥት 18:30 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))
ኤልያስም ሕዝቡን ሁሉ “ወደ እኔ ቅረቡ፤” አላቸው። ሕዝቡም ሁሉ ወደ እርሱ ቀረቡ። ፈርሶ የነበረውንም የእግዚአብሔርን መሠዊያ አበጀ።
1 ነገሥት 18:30 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)
ከዚህ በኋላ ኤልያስ ሰዎቹን “ወደ እኔ ቅረቡ” አላቸው፤ ሁሉም በዙሪያው ተሰበሰቡ፤ እርሱም ፈርሶ የነበረውን የእግዚአብሔር መሠዊያ በማደስ ሠራው።
1 ነገሥት 18:30 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))
ከዚህ በኋላ ኤልያስ ሰዎቹን “ወደ እኔ ቅረቡ” አላቸው፤ ሁሉም በዙሪያው ተሰበሰቡ፤ እርሱም ፈርሶ የነበረውን የጌታ መሠዊያ በማደስ ሠራው።