1 ነገሥት 18:38 - Compare All Versions

1 ነገሥት 18:38 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

እሳ​ትም ከሰ​ማይ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ወረ​ደች፤ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት፥ እን​ጨ​ቱ​ንም፥ ድን​ጋ​ዮ​ቹ​ንም በላች፤ በጕ​ድ​ጓ​ዱም ውስጥ ያለ​ውን ውኃ፥ አፈ​ሩ​ንም ላሰች።

1 ነገሥት 18:38 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

ከዚያም የእግዚአብሔር እሳት ወርዳ መሥዋዕቱን፣ ዕንጨቱን፣ ድንጋዩንና ዐፈሩን ፈጽማ በላች፤ በጕድጓዱ ውስጥ ያለውንም ውሃ ላሰች።

1 ነገሥት 18:38 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

የእግዚአብሔርም እሳት ወደቀች፤ የሚቃጠለውን መሥዋዕቱንም፥ እንጨቱንም፥ ድንጋዮቹንም፥ አፈሩንም በላች፤ በጕድጓዱም ውስጥ ያለውን ውሃ ላሰች።

1 ነገሥት 18:38 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር እሳትን ላከ፤ ያም እሳት መሥዋዕቱን፥ እንጨቱንና ድንጋዩን አቃጠለ፤ ምድሩንም ለበለበ፤ በጒድጓዱ የነበረውንም ውሃ አደረቀ፤

1 ነገሥት 18:38 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

ከዚህ በኋላ ጌታ እሳትን ላከ፤ ያም እሳት መሥዋዕቱን፥ እንጨቱንና ድንጋዩን አቃጠለ፤ ምድሩንም ለበለበ፤ በጉድጓዱ የነበረውንም ውሃ አደረቀ፤