1 ነገሥት 18:39 - Compare All Versions
1 ነገሥት 18:39 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
ሕዝቡም ሁሉ ያን ባዩ ጊዜ በግንባራቸው ተደፍተው፥ “እግዚአብሔር በእውነት እርሱ አምላክ ነው፤ እግዚአብሔር እርሱ አምላክ ነው” አሉ።
1 ነገሥት 18:39 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
ሕዝቡም ሁሉ ይህን ሲያዩ፣ በግንባራቸው ተደፍተው፣ “አምላክ እግዚአብሔር እርሱ እውነተኛ ነው! እግዚአብሔር እርሱ እውነተኛ አምላክ ነው!” አሉ።
1 ነገሥት 18:39 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))
ሕዝቡም ሁሉ ያንን ባዩ ጊዜ በግምባራቸው ተደፍተው “እግዚአብሔር እርሱ አምላክ ነው! እግዚአብሔር እርሱ አምላክ ነው!” አሉ።
1 ነገሥት 18:39 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)
ሰዎቹም ይህን ባዩ ጊዜ በግንባራቸው መሬት ላይ ተደፍተው በመደነቅ “እግዚአብሔር አምላክ ነው! እውነተኛ አምላክ እርሱ ብቻ ነው!” አሉ።
1 ነገሥት 18:39 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))
ሰዎቹም ይህን ባዩ ጊዜ በግንባራቸው መሬት ላይ ተደፍተው በመደነቅ “ጌታ አምላክ ነው! እውነተኛ አምላክ እርሱ ብቻ ነው!” አሉ።