1 ነገሥት 18:43 - Compare All Versions

1 ነገሥት 18:43 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

ብላ​ቴ​ና​ው​ንም፥ “ወጥ​ተህ ወደ ባሕሩ ተመ​ል​ከት” አለው። ብላ​ቴ​ና​ውም ተመ​ል​ክቶ፥ “ምንም የለም” አለ። ኤል​ያ​ስም፥ “ሰባት ጊዜ ተመ​ላ​ለስ” አለው። ብላ​ቴ​ና​ውም ሰባት ጊዜ ተመ​ላ​ለሰ።

1 ነገሥት 18:43 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

አገልጋዩንም፣ “ውጣና ወደ ባሕሩ ተመልከት” አለው። አገልጋዩም ሄዶ ተመለከተና፤ “በዚያ ምንም የለም” አለው። ኤልያስ ሰባት ጊዜ፣ “እንደ ገና ሂድ” አለው።

1 ነገሥት 18:43 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

ብላቴናውንም “ወጥተህ ወደ ባሕሩ ተመልከት፤” አለው። ወጥቶም ተመልክቶም፥ “ምንም የለም፤” አለ። እርሱም “ሰባት ጊዜ ተመላለስ፤” አለው። ብላቴናውም ሰባት ጊዜ ተመላለሰ።

1 ነገሥት 18:43 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

አገልጋዩን፥ “ሂድና ወደ ባሕሩ አቅጣጫ ተመልከት!” አለው። አገልጋዩም ሄዶ ሲመለስ “ምንም ነገር አይታየኝም” አለው፤ አገልጋዩ እየተመላለሰ ያይ ዘንድ ኤልያስ ሰባት ጊዜ አዘዘው፤

1 ነገሥት 18:43 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

አገልጋዩን፥ “ሂድና ወደ ባሕሩ አቅጣጫ ተመልከት!” አለው። አገልጋዩም ሄዶ ሲመለስ “ምንም ነገር አይታየኝም” አለው፤ አገልጋዩ እየተመላለሰ ያይ ዘንድ ኤልያስ ሰባት ጊዜ አዘዘው።