1 ነገሥት 18:44 - Compare All Versions
1 ነገሥት 18:44 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
በሰባተኛውም ጊዜ፥ “እነሆ፥ የሰው ጫማ የምታህል ትንሽ ደመና ከባሕር ውኃ ቋጥራ ስትወጣ አየሁ” አለ። እርሱም፥ “ወጥተህ አክዓብን፦ ዝናብ እንዳይዝህ ሰረገላህን ጭነህ ውረድ በለው” አለ።
1 ነገሥት 18:44 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
በሰባተኛው ጊዜ አገልጋዩ፣ “እነሆ፤ የሰው እጅ የምታህል ትንሽ ደመና ከባሕሩ እየወጣች ነው” አለው። ኤልያስም፣ “ሂድና አክዓብን፣ ‘ዝናቡ ሳያግድህ፣ ሠረገላህን ጭነህ ውረድ’ ብለህ ንገረው” አለው።
1 ነገሥት 18:44 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))
በሰባተኛውም ጊዜ “እነሆ፥ የሰው እጅ የምታህል ታናሽ ደመና ከባሕር ወጣች፤” አለ። እርሱም “ወጥተህ አክዓብን ‘ዝናብ እንዳይከለክልህ ሠረገላን ጭነህ ውረድ፤’ በለው፤” አለ።
1 ነገሥት 18:44 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)
በሰባተኛውም ጊዜ አገልጋዩ ተመልሶ “ከአንድ ሰው መዳፍ የማትበልጥ ትንሽ ደመና ከባሕር ስትወጣ አየሁ” አለው። ኤልያስም “ወደ ንጉሥ አክዓብ ሂድና ‘ዝናቡ ሳያቋርጥህ በፍጥነት ወደ ሠረገላህ ገብተህ ወደ ቤትህ ተመልሰህ ሂድ’ ብለህ ንገረው” ሲል አዘዘው።
1 ነገሥት 18:44 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))
በሰባተኛውም ጊዜ አገልጋዩ ተመልሶ “ከአንድ ሰው መዳፍ የማትበልጥ ትንሽ ደመና ከባሕር ስትወጣ አየሁ” አለው። ኤልያስም “ወደ ንጉሥ አክዓብ ሂድና ‘ዝናቡ ሳያቋርጥህ በፍጥነት ወደ ሠረገላህ ገብተህ ወደ ቤትህ ተመልሰህ ሂድ’ ብለህ ንገረው” ሲል አዘዘው።