1 ነገሥት 19:21 - Compare All Versions

1 ነገሥት 19:21 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

ከእ​ር​ሱም ዘንድ ተመ​ልሶ ሁለ​ቱን በሬ​ዎች ወስዶ አረ​ዳ​ቸው፤ ሥጋ​ቸ​ው​ንም በበ​ሬ​ዎቹ ዕቃ ቀቀ​ለው፤ ለሕ​ዝ​ቡም ሰጣ​ቸው፤ በሉም፤ እር​ሱም ተነ​ሥቶ ኤል​ያ​ስን ተከ​ትሎ ሄደ፤ ያገ​ለ​ግ​ለ​ውም ነበር።

1 ነገሥት 19:21 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

ስለዚህም ኤልሳዕ ትቶት ተመለሰ። ሁለቱን በሬዎቹን ወስዶ ዐረደ፤ የዕርሻ ዕቃውን አንድዶ ሥጋቸውን በመቀቀል ለሕዝቡ ሰጠ፤ እነርሱም በሉ። ከዚያም ኤልያስን ለመከተል ሄደ፤ ረዳቱም ሆነ።

1 ነገሥት 19:21 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

ከእርሱም ዘንድ ተመልሶ ሁለቱን በሬዎች ወስዶ አረዳቸው፤ ሥጋቸውንም በበሬዎቹ ዕቃ ቀቀለው፤ ለሕዝቡም ሰጣቸው፤ በሉም፤ እርሱም ተነሥቶ ኤልያስን ተከትሎ ሄደ፤ ያገለግለውም ነበር።

1 ነገሥት 19:21 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

ከዚህ በኋላ ኤልሳዕ ወደ ጥማድ በሬዎቹ ተመልሶ ዐረዳቸው፤ የተጠመዱበትንም ቀንበር በማንደድ ሥጋቸውን ቀቅሎ ለሰዎቹ አቀረበላቸው፤ እነርሱም በሉ፤ ከዚህ በኋላ ኤልያስን ተከትሎ በመሄድ ረዳቱ ሆነ።

1 ነገሥት 19:21 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

ከዚህ በኋላ ኤልሳዕ ወደ ጥማድ በሬዎቹ ተመልሶ ዐረዳቸው፤ የተጠመዱበትንም ቀንበር በማንደድ ሥጋቸውን ቀቅሎ ለሰዎቹ አቀረበላቸው፤ እነርሱም በሉ፤ ከዚህ በኋላ ኤልያስን ተከትሎ በመሄድ ረዳቱ ሆነ።