1 ነገሥት 19:9 - Compare All Versions

1 ነገሥት 19:9 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

እዚ​ያም ወዳለ ዋሻ ገባ፤ በዚ​ያም አደረ፤ እነ​ሆም፥ “ኤል​ያስ ሆይ! ምን አመ​ጣህ?” የሚል የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ወደ እርሱ መጣ።

1 ነገሥት 19:9 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

በዚያም ወደ አንዲት ዋሻ ገብቶ ዐደረ። የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እርሱ መጣ፤ “ኤልያስ ሆይ፤ እዚህ ምን ታደርጋለህ?” አለው።

1 ነገሥት 19:9 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

እዚያም ወዳለ ዋሻ መጣ፥ በዚያም አደረ። እነሆም “ኤልያስ ሆይ! በዚህ ምን ታደርጋለህ?” የሚል የእግዚአብሔር ቃል ወደ እርሱ መጣ።

1 ነገሥት 19:9 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

እዚያም እንደ ደረሰ ወደ አንድ ዋሻ ገብቶ እዚያ ዐደረ። በድንገትም እግዚአብሔር “ኤልያስ ሆይ! እዚህ ምን ታደርጋለህ?” ሲል ጠየቀው።

1 ነገሥት 19:9 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

እዚያም እንደ ደረሰ ወደ አንድ ዋሻ ገብቶ እዚያ ዐደረ። በድንገትም ጌታ “ኤልያስ ሆይ! እዚህ ምን ታደርጋለህ?” ሲል ጠየቀው።