1 ነገሥት 2:2-4 - Compare All Versions

1 ነገሥት 2:2-4 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

“እኔ የም​ድ​ሩን መን​ገድ ሁሉ እሄ​ዳ​ለሁ፤ በርታ ሰውም ሁን፤ እን​ደ​ማ​ዝ​ዝህ የም​ታ​ደ​ር​ገ​ውን ሁሉ ታውቅ ዘንድ፥ በሙሴ ሕግ የተ​ጻ​ፈ​ውን ሥር​ዐ​ቱ​ንና ትእ​ዛ​ዛ​ቱን፥ ፍር​ዱ​ንና ምስ​ክ​ሩ​ንም ትጠ​ብቅ ዘንድ በመ​ን​ገ​ዱም ትሄድ ዘንድ፥ የአ​ም​ላ​ክ​ህን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ ጠብቅ። ይኸ​ውም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ እኔ፦ ‘ልጆ​ችህ መን​ገ​ዳ​ቸ​ውን ቢጠ​ብቁ፥ በፊ​ቴም በፍ​ጹም ልባ​ቸ​ውና በፍ​ጹም ነፍ​ሳ​ቸው በእ​ው​ነት ቢሄዱ ከእ​ስ​ራ​ኤል ዙፋን ሰው አይ​ጠ​ፋም’ ብሎ የተ​ና​ገ​ረ​ውን ቃል ያጸና ዘንድ ነው።

1 ነገሥት 2:2-4 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

“እነሆ፤ እኔ የምድሩን ሁሉ መንገድ ልሄድ ነው፤ እንግዲህ በርታ፤ ሰውም ሁን። የአምላክህን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ጠብቅ፤ የምታደርገው ሁሉ እንዲከናወንልህ፣ በምትሄድበትም ሁሉ እንዲሳካልህ፣ በሙሴ ሕግ እንደ ተጻፈው በመንገዶቹ ተመላለስ፣ ሥርዐቶቹንና ትእዛዞቹን፣ ሕጎቹንና ደንቦቹን ጠብቅ፤ እግዚአብሔርም፣ ‘ዘሮችህ መንገዳቸውን ቢጠብቁ፣ እንዲሁም በፍጹም ልባቸው፣ በፍጹም ነፍሳቸው በታማኝነት በፊቴ ቢመላለሱ፣ በእስራኤል ዙፋን የሚቀመጥ ሰው ከዘርህ አላሳጣህም’ ሲል የሰጠኝን ተስፋ ይፈጽምልኛል።

1 ነገሥት 2:2-4 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

“እኔ የምድሩን ሁሉ መንገድ እሄዳለሁ፤ በርታ፤ ሰውም ሁን፤ የምታደርገውንና የምትሄድበትን ሁሉ ታከናውን ዘንድ፥ በሙሴ ሕግ እንደ ተጻፈ ሥርዐቱንና ትእዛዛቱን ፍርዱንና ምስክሩንም ትጠብቅ ዘንድ፥ በመንገዱም ትሄድ ዘንድ፥ የአምላክህን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ጠብቅ። ይኸውም ደግሞ እግዚአብሔር ስለ እኔ ‘ልጆችህ መንገዳቸውን ቢጠብቁ፥ በፊቴም በፍጹም ልባቸውና በፍጹም ነፍሳቸው በእውነት ቢሄዱ ከእስራኤል ዙፋን ሰው አይቆረጥብህም፤’ ብሎ የተናገረውን ቃል ያጸና ዘንድ ነው።

1 ነገሥት 2:2-4 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

“እነሆ እኔ ሰው ሁሉ እንደሚሞት የምሞትበት ጊዜ ተቃርቦአል፤ እንግዲህ በርታ! ቈራጥ ሰው ሁን፤ አምላክህ እግዚአብሔር እንድታደርግ የሚያዝህን ሁሉ አድርግ፤ በምትሄድበት ስፍራ ሁሉ የምታደርገው ማናቸውም ነገር እንዲከናወንልህ በሙሴ አማካይነት በተሰጠው ሕግ የተጻፉትን የእግዚአብሔርን ሕግና ትእዛዝ፥ ሥርዓትና ፈቃድ ሁሉ ጠብቅ፤ በዚህ ሁሉ ነገር ታዛዥ ብትሆንለት፥ ‘ዘሮችህ በጥንቃቄ ተጠብቀው ቢኖሩ፥ በፍጹም ልባቸውና በፍጹም ነፍሳቸው በፊቴ በቅንነት ቢመላለሱ፥ በእስራኤል ዙፋን ላይ ነግሦ የሚገዛ ዘር አላሳጣህም’ ብሎ የነገረኝን የተስፋ ቃል ይፈጽማል።

1 ነገሥት 2:2-4 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

“እነሆ እኔ ሰው ሁሉ እንደሚሞት የምሞትበት ጊዜ ተቃርቧል፤ እንግዲህ በርታ! ቆራጥ ሰው ሁን፤ አምላክህ ጌታ እንድታደርግ የሚያዝህን ሁሉ አድርግ፤ በምትሄድበት ስፍራ ሁሉ የምታደርገው ማንኛውም ነገር እንዲከናወንልህ በሙሴ አማካይነት በተሰጠው ሕግ የተጻፉትን የእግዚአብሔርን ሕግና ትእዛዝ፥ ሥርዓትና ፈቃድ ሁሉ ጠብቅ፤ በዚህ ሁሉ ነገር ታዛዥ ብትሆንለት፥ ‘ዘሮችህ በጥንቃቄ ተጠብቀው ቢኖሩ፥ በፍጹም ልባቸውና በፍጹም ነፍሳቸው በፊቴ በቅንነት ቢመላለሱ፥ በእስራኤል ዙፋን ላይ ነግሦ የሚገዛ ዘር አላሳጣህም’ ብሎ ጌታ የነገረኝን የተስፋ ቃል ይፈጽማል።