1 ነገሥት 3:13 - Compare All Versions

1 ነገሥት 3:13 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

ደግ​ሞም ከነ​ገ​ሥ​ታት የሚ​መ​ስ​ልህ ማንም እን​ዳ​ይ​ኖር ያል​ለ​መ​ን​ኸ​ውን ባለ​ጠ​ግ​ነ​ትና ክብር ሰጥ​ቼ​ሃ​ለሁ።

1 ነገሥት 3:13 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

ከዚህም በላይ አንተ ያልጠየቅኸውን ብልጽግናና ክብር እሰጥሃለሁ፤ ይኸውም በሕይወት ዘመንህ የሚተካከልህ ማንም ንጉሥ እንዳይኖር ነው።

1 ነገሥት 3:13 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

ደግሞም ከነገሥታት የሚመስልህ ማንም እንዳይኖር ያልለመንኸውን ባለጠግነትና ክብር ሰጥቼሃለሁ።

1 ነገሥት 3:13 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

ከዚህም በላይ አንተ ያልጠየቅከውንም ሁሉ ጨምሬ እሰጥሃለሁ፤ ይኸውም በዘመንህ ማንኛውም ሌላ ንጉሥ ያላገኘውን ብልጽግናና ክብር አበዛልሃለሁ።

1 ነገሥት 3:13 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

ከዚህም በላይ አንተ ያልጠየቅከውንም ሁሉ ጨምሬ እሰጥሃለሁ፤ ይኸውም በዘመንህ ማንኛውም ሌላ ንጉሥ ያላገኘውን ብልጽግናና ክብር አበዛልሃለሁ።