1 ነገሥት 3:7 - Compare All Versions

1 ነገሥት 3:7 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

አሁ​ንም አቤቱ አም​ላኬ ሆይ፥ እኔን ባሪ​ያ​ህን በአ​ባቴ በዳ​ዊት ፋንታ አን​ግ​ሠ​ኸ​ኛል፤ እኔም መው​ጫ​ዬ​ንና መግ​ቢ​ያ​ዬን የማ​ላ​ውቅ ታናሽ ብላ​ቴና ነኝ።

1 ነገሥት 3:7 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

“አሁንም እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፤ ባሪያህ በአባቴ በዳዊት እግር ተተክቼ እንድነግሥ አድርገሃል፤ እኔ ግን ገና ትንሽ ልጅ ስለ ሆንሁ፣ መውጫና መግቢያዬን አላውቅም።

1 ነገሥት 3:7 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

አሁንም፥ አቤቱ አምላኬ ሆይ! እኔን ባሪያህን በአባቴ በዳዊት ፋንታ አንግሠኸኛል፤ እኔም መውጫውንና መግቢያን የማላውቅ ታናሽ ብላቴና ነኝ።

1 ነገሥት 3:7 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

እግዚአብሔር አምላክ ሆይ! እነሆ እኔ በዕድሜ አነስተኛ ነኝ፤ የአመራር ልምድም የለኝም፤ አንተ ግን በአባቴ እግር ተተክቼ እንድነግሥ ፈቃድህ ሆኖአል፤

1 ነገሥት 3:7 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

አቤቱ፥ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ! እነሆ እኔ በዕድሜ አነስተኛ ነኝ፤ የአመራር ልምድም የለኝም፤ አንተ ግን በአባቴ እግር ተተክቼ እንድነግሥ ፈቃድህ ሆኖአል።