1 ጴጥሮስ 3:15-16
1 ጴጥሮስ 3:15-16 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ዳሩ ግን ጌታን እርሱም ክርስቶስ በልባችሁ ቀድሱት። በእናንተ ስላለ ተስፋ ምክንያትን ለሚጠይቁዋችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት ዘወትር የተዘጋጃችሁ ሁኑ፤ ነገር ግን በየዋህነትና በፍርሃት ይሁን። በክርስቶስ ያለውን መልካሙን ኑሮአችሁን የሚሳደቡ ሰዎች ክፉን እንደምታደርጉ በሚያሙበት ነገር እንዲያፍሩ በጎ ሕሊና ይኑራችሁ።
Share
1 ጴጥሮስ 3 ያንብቡ1 ጴጥሮስ 3:15-16 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ጌታ ክርስቶስን በልባችሁ አክብሩት፤ ለሕይወታችሁም ጌታ አድርጉት፤ በእናንተ ስላለውም ተስፋ ለሚጠይቃችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት ሁልጊዜ ዝግጁዎች ሁኑ። መልሳችሁ ግን በገርነትና በአክብሮት ይሁን፤ የክርስቶስ በመሆናችሁ ባላችሁ መልካም ጠባይ ላይ ክፉ የሚናገሩ ሰዎች በክፉ ንግግራቸው እንዲያፍሩ መልካም ኅሊና ይኑራችሁ።
Share
1 ጴጥሮስ 3 ያንብቡ