2 ነገሥት 2:10 - Compare All Versions

2 ነገሥት 2:10 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

ኤል​ያ​ስም፥ “አስ​ቸ​ጋሪ ነገር ለም​ነ​ሃል፤ ነገር ግን ከአ​ንተ ዘንድ በተ​ወ​ሰ​ድሁ ጊዜ ብታ​የኝ ይሆ​ን​ል​ሃል፤ አለ​ዚያ ግን አይ​ሆ​ን​ል​ህም” አለው።

2 ነገሥት 2:10 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

ኤልያስም፣ “አስቸጋሪ ነገር ጠይቀሃል፤ ይሁን እንጂ እኔ ከአንተ ስወሰድ ብታየኝ፣ እንዳልከው ይሆንልሃል፤ አለዚያ ግን አይሆንም” አለው።

2 ነገሥት 2:10 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

እርሱም “አስቸጋሪ ነገር ለምነሃል፤ ነገር ግን ከአንተ ዘንድ በተወሰድሁ ጊዜ ብታየኝ ይሆንልሃል፤ አለዚያ ግን አይሆንልህም፤” አለ።

2 ነገሥት 2:10 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

ኤልያስም “ያቀረብከው ጥያቄ ከባድ ነው፤ ነገር ግን እኔ ከአንተ ተለይቼ ወደ ሰማይ ስወሰድ ብታየኝ ይህን የጠየቅኸውን ስጦታ መቀበል ትችላለህ፤ ባታየኝ ግን ልታገኘው አትችልም” ሲል መለሰለት።

2 ነገሥት 2:10 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

ኤልያስም “ያቀረብከው ጥያቄ ከባድ ነው፤ ነገር ግን እኔ ከአንተ ተለይቼ ወደ ሰማይ ስወሰድ ብታየኝ ይህን የጠየቅኸውን ስጦታ መቀበል ትችላለህ፤ ባታየኝ ግን ልታገኘው አትችልም” ሲል መለሰለት።