2 ነገሥት 2:11 - Compare All Versions

2 ነገሥት 2:11 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

ሁለ​ቱም እየ​ተ​ነ​ጋ​ገሩ ሲሄዱ፥ እነሆ፥ የእ​ሳት ሰረ​ገ​ላና የእ​ሳት ፈረ​ሶች በሁ​ለቱ መካ​ከል ገብ​ተው ከፈ​ሉ​አ​ቸው፤ ኤል​ያ​ስም በዐ​ውሎ ነፋስ ንው​ጽ​ው​ጽታ ወደ ሰማይ ወጣ።

2 ነገሥት 2:11 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

እያዘገሙም ሲነጋገሩ ሳለ፣ የእሳት ሠረገላና የእሳት ፈረሶች ድንገት በመካከላቸው ገብተው ሁለቱን ለዩአቸው፤ ኤልያስም በዐውሎ ነፋስ ወደ ሰማይ ዐረገ።

2 ነገሥት 2:11 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

ሲሄዱም፥ እያዘገሙም ሲጫወቱ፥ እነሆ፥ የእሳት ሠረገላና የእሳት ፈረሶች በመካከላቸው ገብተው ከፈሉአቸው፤ ኤልያስም በዐውሎ ነፋስ ወደ ሰማይ ወጣ።

2 ነገሥት 2:11 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

እየተነጋገሩ እርምጃቸውን ቀጠሉ፤ ከዚያም በኋላ የእሳት ፈረሶች የሚስቡአቸው የእሳት ሠረገሎች ድንገት በመካከላቸው ገብተው ሁለቱን ለዩአቸው፤ ኤልያስም በዐውሎ ነፋስ ወደ ሰማይ ተወሰደ።

2 ነገሥት 2:11 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

እየተነጋገሩ እርምጃቸውን ቀጠሉ፤ ከዚያም በኋላ የእሳት ፈረሶች የሚስቡአቸው የእሳት ሠረገሎች ድንገት በመካከላቸው ገብተው ሁለቱን ለዩአቸው፤ ኤልያስም በዐውሎ ነፋስ ወደ ሰማይ ተወሰደ።