2 ነገሥት 2:12 - Compare All Versions
2 ነገሥት 2:12 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
ኤልሳዕም አይቶ፥ “አባቴ! አባቴ ሆይ! የእስራኤል ኀይላቸውና ጽንዓቸው፥” ብሎ ጮኸ። ከዚያም ወዲያ ዳግመኛ አላየውም፤ ልብሱንም ይዞ ከሁለት ቀደደው።
2 ነገሥት 2:12 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
ኤልሳዕም ይህን አይቶ፣ “አባቴ አባቴ የእስራኤል ሠረገሎችና ፈረሰኞች!” ብሎ ጮኸ፤ ዳግመኛም ኤልያስን አላየውም፤ ከዚያም የገዛ ልብሱን ይዞ ከሁለት ቦታ ቀደደው።
2 ነገሥት 2:12 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))
ኤልሳዕም አይቶ፥ “አባቴ አባቴ ሆይ! የእስራኤል ሠረገላና ፈረሰኞች!” ብሎ ጮኸ። ከዚያም ወዲያ አላየውም፤ ልብሱንም ይዞ ከሁለት ተረተረው።
2 ነገሥት 2:12 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)
ኤልሳዕም ይህን ሁሉ እያየ “የእስራኤል ሠረገሎችና ፈረሰኞች የሆንክ አባቴ ሆይ! አባቴ ሆይ!” እያለ ወደ ኤልያስ ጮኸ፤ ከዚያም በኋላ ኤልያስን ዳግመኛ አላየውም። ኤልሳዕም ከሐዘን ብዛት የተነሣ ልብሱን ከሁለት ቀደደ፤
2 ነገሥት 2:12 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))
ኤልሳዕም ይህን ሁሉ እያየ “የእስራኤል ሠረገሎችና ፈረሰኞች የሆንክ አባቴ ሆይ! አባቴ ሆይ!” እያለ ወደ ኤልያስ ጮኸ፤ ከዚያም በኋላ ኤልያስን ዳግመኛ አላየውም። ኤልሳዕም ከኀዘን ብዛት የተነሣ ልብሱን ከሁለት ቀደደ፤