2 ነገሥት 23:25 - Compare All Versions

2 ነገሥት 23:25 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

እንደ ሙሴም ሕግ ሁሉ በፍ​ጹም ልቡ በፍ​ጹ​ምም ነፍሱ በፍ​ጹ​ምም ኀይሉ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​መ​ለሰ እንደ እርሱ ያለ ንጉሥ ከእ​ርሱ አስ​ቀ​ድሞ አል​ነ​በ​ረም፤ እንደ እር​ሱም ያለ ንጉሥ ከእ​ርሱ በኋላ አል​ተ​ነ​ሣም።

2 ነገሥት 23:25 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

በሙሴ ሕግ በተጻፈው መሠረት በፍጹም ልቡ፣ በፍጹም ነፍሱ፣ በፍጹም ኀይሉ ወደ እግዚአብሔር የተመለሰ፣ እንደ ኢዮስያስ ያለ ንጉሥ፣ ከርሱ በፊትም ሆነ ከርሱ በኋላ ፈጽሞ አልተነሣም።

2 ነገሥት 23:25 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

እንደ ሙሴም ሕግ ሁሉ በፍጹም ልቡ በፍጹምም ነፍሱ በፍጹምም ኀይሉ ወደ እግዚአብሔር የተመለሰ እንደ እርሱ ያለ ንጉሥ ከእርሱ አስቀድሞ አልነበረም፤ እንደ እርሱም ያለ ንጉሥ ከእርሱ በኋላ አልተነሣም።

2 ነገሥት 23:25 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

ለኦሪት ሕግ በመታዘዝ በፍጹም ልቡ፥ በፍጹም ነፍሱና በፍጹም ኀይሉ እግዚአብሔርን ያገለገለ እንደ ኢዮስያስ ያለ ንጉሥ ከእርሱም በፊት ሆነ ከእርሱ ወዲህ ከቶ አልነበረም።

2 ነገሥት 23:25 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

ለኦሪት ሕግ በመታዘዝ በፍጹም ልቡ፥ በፍጹም ነፍሱና በፍጹም ኃይሉ እግዚአብሔርን ያገለገለ እንደ ኢዮስያስ ያለ ንጉሥ ከእርሱም በፊት ሆነ ከእርሱ ወዲህ ከቶ አልነበረም።