2 ነገሥት 4:2 - Compare All Versions
2 ነገሥት 4:2 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
ኤልሳዕም፥ “አደርግልሽ ዘንድ ምን ትሻለሽ? በቤትሽም ያለውን ንገሪኝ” አላት። እርስዋም፥ “ለእኔ ለአገልጋይህ ከዘይት ማሰሮ በቀር በቤቴ አንዳች የለኝም” አለችው።
2 ነገሥት 4:2 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
ኤልሳዕም፣ “ታዲያ እኔ ምን እንዳደርግልሽ ትፈልጊያለሽ? በቤትሽ ምን እንዳለ ንገሪኝ” አላት። እርሷም፣ “አገልጋይህ ከጥቂት ዘይት በቀር በቤቷ ምንም ነገር የላትም” አለች።
2 ነገሥት 4:2 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))
ኤልሳዕም “አደርግልሽ ዘንድ ምን ትሻለሽ? በቤትሽ ያለውን ንገሪኝ፤” አላት። እርስዋም “ለእኔ ለባሪያህ ከዘይት ማሰሮ በቀር በቤቴ አንዳች የለኝም፤” አለች።
2 ነገሥት 4:2 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)
ኤልሳዕም “ታዲያ ምን እንዳደርግልሽ ትፈልጊያለሽ? በቤትሽም ምን እንዳለሽ ንገሪኝ” ሲል ጠየቃት። እርስዋም “በትንሽ ማሰሮ ከሚገኝ የወይራ ዘይት በቀር ሌላ ምንም የለኝም” ስትል መለሰች።
2 ነገሥት 4:2 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))
ኤልሳዕም “ታዲያ ምን እንዳደርግልሽ ትፈልጊያለሽ? በቤትሽም ምን እንዳለሽ ንገሪኝ” ሲል ጠየቃት። እርሷም “በትንሽ ማሰሮ ከሚገኝ የወይራ ዘይት በቀር ሌላ ምንም የለኝም” ስትል መለሰች።