2 ነገሥት 4:34 - Compare All Versions
2 ነገሥት 4:34 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
መጥቶም በሕፃኑ ላይ ተኛ፤ አፉንም በአፉ፥ ዐይኖቹንም በዐይኖቹ፥ እጆቹንም በእጆቹ ላይ አድርጎ ተጋደመበት፤ የሕፃኑም ሰውነት ሞቀ።
2 ነገሥት 4:34 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
በዐልጋው ላይ ወጥቶም በልጁ ላይ ተጋደመና አፉን በአፉ፣ ዐይኑን በዐይኑ፣ እጁን በእጁ ላይ አደረገ። ሙሉ በሙሉ እንደተዘረጋበትም፣ የልጁ ሰውነት መሞቅ ጀመረ።
2 ነገሥት 4:34 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))
መጥቶም በሕፃኑ ላይ ተኛ፤ አፉንም በአፉ፥ ዐይኑንም በዓይኑ፥ እጁንም በእጁ ላይ አድርጎ ተጋደመበት፤ የሕፃኑም ገላ ሞቀ።
2 ነገሥት 4:34 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)
ከዚህም በኋላ አፉን ከአፉ፥ ዐይኖቹን ከዐይኖቹ፥ እጆቹን ከእጆቹ ጋር ገጥሞ በልጁ ሬሳ ላይ ተጋደመ፤ ኤልሳዕም ተዘርግቶ እንደ ተጋደመበት የልጁ ሰውነት መሞቅ ጀመረ።
2 ነገሥት 4:34 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))
ከዚህም በኋላ አፉን ከአፉ፥ ዐይኖቹን ከዐይኖቹ፥ እጆቹን ከእጆቹ ጋር ገጥሞ በልጁ ሬሳ ላይ ተጋደመ፤ ኤልሳዕም ተዘርግቶ እንደ ተጋደመበት የልጁ ሰውነት መሞቅ ጀመረ።