2 ነገሥት 4:6 - Compare All Versions
2 ነገሥት 4:6 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
ከዚህም በኋላ ልጆችዋን፥ “ደግሞ ማድጋ አምጡልኝ” አለቻቸው፤ እነርሱም፥ “ሌላ ማድጋ የለም” አሏት፤ ዘይቱም ቆመ።
2 ነገሥት 4:6 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
ማድጋዎቹ ሁሉ ከሞሉ በኋላ ልጇን፣ “ሌላ ማድጋ አምጣ” አለችው። እርሱ ግን፣ “ምንም የቀረ ማድጋ የለም” ሲል መለሰላት። ከዚያም ዘይቱ መውረዱን አቆመ።
2 ነገሥት 4:6 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))
ማድጋዎቹም በሞሉ ጊዜ ልጅዋን “ደግሞም ማድጋ አምጣልኝ፤” አለችው፤ እርሱም “ሌላ ማድጋ የለም፤” አላት፤ ዘይቱም ቆመ።
2 ነገሥት 4:6 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)
ማድጋዎቹንም ሁሉ ከሞሉ በኋላ “ሌላ ትርፍ የለም ወይ?” ስትል ጠየቀች፤ ከልጆችዋም አንዱ “ሌላ ማድጋ የለም” ሲል መለሰላት። ከዚያም በኋላ ዘይቱ መውረዱን አቆመ፤
2 ነገሥት 4:6 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))
ማድጋዎቹንም ሁሉ ከሞሉ በኋላ “ሌላ ትርፍ የለም ወይ?” ስትል ጠየቀች፤ ከልጆችዋም አንዱ “ሌላ ማድጋ የለም” ሲል መለሰላት። ከዚያም በኋላ ዘይቱ መውረዱን አቆመ፤