2 ነገሥት 5:1 - Compare All Versions

2 ነገሥት 5:1 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

የሶ​ርያ ንጉሥ ሠራ​ዊት አለቃ ንዕ​ማ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ርሱ እጅ ለሶ​ርያ ደኅ​ን​ነ​ትን ስለ ሰጠ፥ በጌ​ታው ዘንድ ታላ​ቅና ክቡር ሰው ነበረ፤ ሰው​ዬ​ውም ጽኑዕ፥ ኀያል ነበረ፤ ነገር ግን ለም​ጻም ነበረ።

2 ነገሥት 5:1 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

በዚህ ጊዜ ንዕማን የሶርያ ንጉሥ ጦር አዛዥ ነበረ፤ እግዚአብሔር በዚህ ሰው አማካይነት፣ ሶርያ ድልን እንድትጐናጸፍ ስላደረጋት በጌታው ዘንድ ታላቅና የተከበረ ሰው ነበር። ጀግና ወታደር ቢሆንም ለምጽ ወጥቶበት ነበር።

2 ነገሥት 5:1 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

የሶርያ ንጉሥ ሠራዊት አለቃ ንዕማን እግዚአብሔር በእርሱ እጅ ለሶርያ ደኅንነትን ስለ ሰጠ በጌታው ዘንድ ታላቅ ክቡር ሰው ነበረ፤ ደግሞም ጽኑዕ ኀያል ነበረ፤ ነገር ግን ለምጻም ነበረ።

2 ነገሥት 5:1 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

እግዚአብሔር በንዕማን አማካይነት ለሶርያ ሠራዊት ድልን ስለ አጐናጸፈ፥ የሶርያ ጦር አዛዥ የነበረው ንዕማን በሶርያ ንጉሥ ዘንድ እጅግ የተከበረና የተወደደ ባለሟል ነበር፤ ታዲያ ንዕማን ጀግና ወታደር ሆኖ ሳለ፥ በቈዳ በሽታ ይሠቃይ ነበር።

2 ነገሥት 5:1 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

እግዚአብሔር በንዕማን አማካይነት ለሶርያ ሠራዊት ድልን ስለ አጐናጸፈ፥ የሶርያ ጦር አዛዥ የነበረው ንዕማን በሶርያ ንጉሥ ዘንድ እጅግ የተከበረና የተወደደ ባለሟል ነበር፤ ታዲያ ንዕማን ጀግና ወታደር ሆኖ ሳለ፥ በቆዳ በሽታ ይሠቃይ ነበር።