2 ነገሥት 5:13 - Compare All Versions

2 ነገሥት 5:13 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹም ወደ እርሱ መጥ​ተው፥ “ነቢዩ ታላቅ ነገር ቢነ​ግ​ርህ ባደ​ረ​ግ​ኸው ነበር፤ ይል​ቁ​ንስ፦ ተጠ​መ​ቅና ንጹሕ ሁን ቢልህ እን​ዴት ነዋ!” ብለው ተና​ገ​ሩት።

2 ነገሥት 5:13 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

የንዕማን አገልጋዮች ግን ወደ እርሱ ቀርበው፣ “አባት ሆይ፤ ነቢዩ ከዚህ ከበድ ያለ ነገር እንድታደርግ ቢነግርህ ኖሮ አታደርገውም ነበርን? ታዲያ፣ ‘ታጠብና ንጻ’ ቢልህ ምኑ አስቸገረህ?” አሉት።

2 ነገሥት 5:13 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

ባሪያዎቹም ቀርበው “አባት ሆይ! ነቢዩ ታላቅ ነገርስ እንኳ ቢነግርህ ኖሮ ባደረግኸው ነበር፤ ይልቁንስ ‘ታጠብና ንጹሕ ሁን፤’ ቢልህ እንዴት ነዋ!” ብለው ተናገሩት።

2 ነገሥት 5:13 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

የንዕማንም አሽከሮች ወደ እርሱ ቀረብ ብለው፥ “ጌታችን ሆይ፥ ነቢዩ ሌላ ከባድ ነገር እንድታደርግ ቢያዝህ ኖሮ ትፈጽመው ነበር፤ ታዲያ ነቢዩ ባዘዘህ መሠረት ታጥበህ ከበሽታህ መንጻት ምን ይከብድሃል?” አሉት።

2 ነገሥት 5:13 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

የንዕማንም አሽከሮች ወደ እርሱ ቀረብ ብለው፥ “ጌታችን ሆይ፥ ነቢዩ ሌላ ከባድ ነገር እንድታደርግ ቢያዝህ ኖሮ ትፈጽመው ነበር፤ ታዲያ ነቢዩ ባዘዘህ መሠረት ታጥበህ ከበሽታህ መንጻት ምን ይከብድሃል?” አሉት።