2 ነገሥት 6:15 - Compare All Versions

2 ነገሥት 6:15 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

የኤ​ል​ሳ​ዕም ሎሌ ማለዳ ነቃ፤ ተነ​ሥ​ቶም በወጣ ጊዜ፥ እነሆ፥ በከ​ተ​ማ​ዪቱ ዙሪያ ጭፍ​ሮች ከተ​ማ​ዋን ከብ​በ​ዋት አየ። ፈረ​ሶ​ችና ሰረ​ገ​ሎ​ችም ነበሩ። ሎሌ​ውም፥ “ጌታዬ ሆይ፥ ወዮ! ምን እና​ድ​ርግ?” አለው።

2 ነገሥት 6:15 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

የእግዚአብሔር ሰው አገልጋይ በማለዳ ተነሥቶ ወደ ውጭ ሲወጣ፣ በፈረሶችና በሠረገሎች የተጠናከረ ሰራዊት ከተማዪቱን ከብቧት ነበር። አገልጋዩም “ጌታዬ ሆይ፤ ምን ማድረግ ይሻለናል?” ሲል ጠየቀ።

2 ነገሥት 6:15 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

የእግዚአብሔር ሰው ሎሌ ማለዳ ተነሥቶ በወጣ ጊዜ፥ እነሆ፥ በከተማይቱ ዙሪያ ጭፍራና ፈረሶች ሠረገሎችም ነበሩ። ሎሌውም “ጌታዬ ሆይ! ወዮ! ምን እናደርጋለን?” አለው።

2 ነገሥት 6:15 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

በማግስቱም ማለዳ የኤልሳዕ አገልጋይ ከመኝታው ተነሥቶ፥ ከቤት ሲወጣ በፈረሶችና በሠረገሎች የታጀቡ የሶርያ ወታደሮች ከተማይቱን መክበባቸውን አየ፤ ወደ ኤልሳዕም ተመልሶ ድምፁን ከፍ በማድረግ “ጌታዬ ወዮ! ምን ማድረግ ይሻለናል?” ሲል ጠየቀው።

2 ነገሥት 6:15 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

በማግስቱም ማለዳ የኤልሳዕ አገልጋይ ከመኝታው ተነሥቶ፥ ከቤት ሲወጣ በፈረሶችና በሠረገሎች የታጀቡ የሶርያ ወታደሮች ከተማይቱን መክበባቸውን አየ፤ ወደ ኤልሳዕም ተመልሶ ድምፁን ከፍ በማድረግ “ጌታዬ ወዮ! ምን ማድረግ ይሻለናል?” ሲል ጠየቀው።