2 ነገሥት 6:5 - Compare All Versions
2 ነገሥት 6:5 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
ከእነርሱም አንዱ ዛፉን ሲቈርጥ የምሳሩ ብረት ወልቆ ወደ ውኃው ውስጥ ወደቀ፤ እርሱም፥ “ጌታዬ ሆይ፥ ወየው! ወየው! የተዋስሁት ነበር” ብሎ ጮኸ።
2 ነገሥት 6:5 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
ከእነርሱም አንዱ ዛፍ እየቈረጠ ሳለ፣ መጥረቢያው በርሮ ከውሃው ውስጥ ወደቀ፤ እርሱም፣ “ወየው ጌታዬ፤ የተውሶ መጥረቢያ እኮ ነው!” ብሎ ጮኸ።
2 ነገሥት 6:5 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))
ከእነርሱም አንዱ ምሰሶውን ሲቆርጥ የምሳሩ ብረት ወደ ውሃው ውስጥ ወደቀ፤ እርሱም “ጌታዬ ሆይ! ወየው! ወየው! የተዋስሁት ነበረ፤” ብሎ ጮኸ።
2 ነገሥት 6:5 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)
ከእነርሱም አንዱ ዛፍ በመቊረጥ ላይ ሳለ በድንገት መጥረቢያው ከዛቢያው ላይ ወድቆ ውሃ ውስጥ ገባ፤ እርሱም ድምፁን ከፍ አድርጎ በመጮኽ “ጌታዬ ሆይ! እንግዲህ ምን አደርጋለሁ? መጥረቢያው የተውሶ ነው!” ሲል ለኤልሳዕ ነገረው።
2 ነገሥት 6:5 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))
ከእነርሱም አንዱ ዛፍ በመቁረጥ ላይ ሳለ በድንገት መጥረቢያው ከዛቢያው ላይ ወድቆ ውሃ ውስጥ ገባ፤ እርሱም ድምፁን ከፍ አድርጎ በመጮኽ “ጌታዬ ሆይ! እንግዲህ ምን አደርጋለሁ? መጥረቢያው የተውሶ ነው!” ሲል ለኤልሳዕ ነገረው።