2 ሳሙኤል 24:24
2 ሳሙኤል 24:24 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ንጉሡም ኦርናን፥ “እንዲህ አይደለም፤ ነገር ግን በዋጋ ከአንተ እገዛለሁ፤ ለአምላኬም ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት ያለ ዋጋ አላቀርብም” አለው። ዳዊትም አውድማውንና በሬዎቹን በአምሳ ሰቅል ብር ገዛ።
2 ሳሙኤል 24:24 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ንጉሡ ግን ኦርናን፣ “እንዲህ አይደረግም፤ ዋጋውን ላንተ መክፈል አለብኝ፤ ለአምላኬም ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት ያለ ዋጋ አላቀርብም” አለው። ስለዚህም ዳዊት ዐውድማውንና በሬዎቹን በዐምሳ ሰቅል ብር ገዛ፤
2 ሳሙኤል 24:24 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ንጉሡም ኦርናን፦ እንዲህ አይደለም፥ ነገር ግን በዋጋ ከአንተ እገዛለሁ፥ ለአምላኬም ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት ያለዋጋ አላቀርብም አለው። ዳዊትም አውድማውንና በሬዎቹን በአምሳ ሰቅል ብር ገዛ።