ሐዋርያት ሥራ 2:45-46 - ሁሉንም ስሪቶች ያወዳድሩ

ሐዋርያት ሥራ 2:45-46 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

ሀብታቸውንና ንብረታቸውንም እየሸጡ ለእያንዳንዱ ሰው የሚያስፈልገውን ያህል ይሰጡት ነበር። በየዕለቱ በቤተ መቅደስ በአንድነት እየተገናኙ፣ በቤታቸውም እንጀራ እየቈረሱ በደስታና በቀና ልብ ይመገቡ ነበር፤

ሐዋርያት ሥራ 2:45-46 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

ዕርሻቸውንና ሀብታቸውን እየሸጡ ገንዘቡን ለእያንዳንዱ እንደሚያስፈልገው ያከፋፍሉ ነበር። በየቀኑ በቤተ መቅደስ በአንድነት ይሰበሰቡ ነበር፤ በቤታቸውም እንጀራ እየቈረሱ በደስታና በጥሩ ልብ ይመገቡ ነበር፤

ሐዋርያት ሥራ 2:45-46 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

መሬ​ታ​ቸ​ው​ንና ጥሪ​ታ​ቸ​ው​ንም እየ​ሸጡ ለእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ እን​ደ​ሚ​ያ​ሻው ይሰጡ ነበር። ሁል​ጊ​ዜም አንድ ልብ ሆነው በቤተ መቅ​ደስ ያገ​ለ​ግሉ ነበር፤ በቤ​ትም ኅብ​ስ​ትን ይቈ​ርሱ ነበር፤ በደ​ስ​ታና በልብ ቅን​ን​ነ​ትም ምግ​ባ​ቸ​ውን ይመ​ገቡ ነበር።

ሐዋርያት ሥራ 2:45-46 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

ያላቸውንም ሁሉ አንድነት አደረጉ። መሬታቸውንና ጥሪታቸውንም እየሸጡ፥ ማንኛውም እንደሚፈልግ ለሁሉ ያካፍሉት ነበር። በየቀኑም በአንድ ልብ ሆነው በመቅደስ እየተጉ በቤታቸውም እንጀራ እየቈረሱ፥ በደስታና በጥሩ ልብ ምግባቸውን ይመገቡ ነበር፤

ሐዋርያት ሥራ 2:45-46 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

ያላቸውንም ሁሉ አንድነት አደረጉ። መሬታቸውንና ጥሪታቸውንም እየሸጡ፥ ማንኛውም እንደሚፈልግ ለሁሉ ያካፍሉት ነበር። በየቀኑም በአንድ ልብ ሆነው በመቅደስ እየተጉ በቤታቸውም እንጀራ እየቆረሱ፥ በደስታና በጥሩ ልብ ምግባቸውን ይመገቡ ነበር፤