ሐዋርያት ሥራ 4:6 - ሁሉንም ስሪቶች ያወዳድሩ

ሐዋርያት ሥራ 4:6 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

ሊቀ ካህናቱ ሐና፣ ቀያፋ፣ ዮሐንስ፣ እስክንድሮስና የሊቀ ካህናቱ ቤተ ዘመዶች ሁሉ በዚያ ተገኝተው ነበር።

ሐዋርያት ሥራ 4:6 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

ከተሰበሰቡት ሰዎች መካከል የካህናት አለቃው ሐናና ቀያፋ፥ ዮሐንስና እስክንድሮስ፥ የካህናት አለቃው ቤተሰቦች ሁሉ ይገኙባቸዋል፤

ሐዋርያት ሥራ 4:6 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

ሊቀ ካህ​ናቱ ሐና፥ ቀያ​ፋም፥ ዮሐ​ን​ስና እለ​እ​ስ​ክ​ን​ድ​ሮ​ስም፥ የሊቀ ካህ​ና​ቱም ወገን ሁሉ ከእ​ነ​ርሱ ጋር ነበሩ።

ሐዋርያት ሥራ 4:5-6 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

በነገውም አለቆቻቸውና ሽማግሌዎች ጻፎችም ሊቀ ካህናቱ ሐናም ቀያፋም ዮሐንስም እስክንድሮስም የሊቀ ካህናቱም ዘመዶች የነበሩት ሁሉ በኢየሩሳሌም ተሰበሰቡ፤

ሐዋርያት ሥራ 4:5-6 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

በነገውም አለቆቻቸውና ሽማግሌዎች ጻፎችም ሊቀ ካህናቱ ሐናም ቀያፋም ዮሐንስም እስክንድሮስም የሊቀ ካህናቱም ዘመዶች የነበሩት ሁሉ በኢየሩሳሌም ተሰበሰቡ፤