ቈላስይስ 1:25-29

ቈላስይስ 1:25-29 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

ስለ እና​ንተ በሰ​ጠኝ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሥር​ዐት እኔ መል​እ​ክ​ተኛ ሆኜ የተ​ሾ​ም​ሁ​ላት። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ና​ገ​ረ​ውን፥ ዓለም ሳይ​ፈ​ጠር፥ ሰውም ሳይ​ፈ​ጠር ተሰ​ውሮ የነ​በ​ረ​ውን ምክ​ሩን እፈ​ጽም ዘንድ። ዛሬ ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የዚ​ህን ምክር የክ​ብር ባለ​ጸ​ግ​ነት በአ​ሕ​ዛብ ላይ እን​ዲ​ገ​ል​ጽ​ላ​ቸው ለፈ​ቀ​ደ​ላ​ቸው ለቅ​ዱ​ሳን ተገ​ለ​ጠ​ላ​ቸው፤ የም​ን​ከ​ብ​ር​በት አለ​ኝ​ታ​ችን በእ​ና​ንተ አድሮ ያለ ክር​ስ​ቶስ ነውና። እር​ሱም ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን በማ​መን ፍጹም የሚ​ሆ​ነ​ውን ሰው እና​ቀ​ር​በው ዘንድ፥ እኛ የም​ና​ስ​ተ​ም​ር​ለት፥ ሰውን ሁሉ ወደ እርሱ የም​ን​ጠ​ራ​ለ​ትና የም​ን​ገ​ሥ​ጽ​ለት፥ ሥራ​ው​ንም በጥ​በብ ሁሉ የም​ን​ና​ገ​ር​ለት ነው። በኀ​ይሉ እን​ደ​ሚ​ረ​ዳኝ እንደ ረድ​ኤቱ መጠን ስለ እርሱ እደ​ክ​ማ​ለሁ፤ እጋ​ደ​ላ​ለ​ሁም።