የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ቈላስይስ 4:7-14

ቈላስይስ 4:7-14 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

ቲኪቆስ ስላለሁበት ሁኔታ በሙሉ ይነግራችኋል፤ እርሱ የተወደደ ወንድምና ታማኝ አገልጋይ፣ በጌታም ዐብሮኝ ባሪያ ነው። ስላለንበት ሁኔታ እንድታውቁና ልባችሁንም እንዲያጽናና ለዚህ ጕዳይ ወደ እናንተ እልከዋለሁ፤ እርሱም ከእናንተ ወገን ከሆነው ከታማኙና ከተወዳጁ ወንድማችን ከአናሲሞስ ጋራ ወደ እናንተ ይመጣል፤ እነርሱም እዚህ ስላለው ሁኔታ ሁሉ ይነግሯችኋል። ዐብሮኝ የታሰረው አርስጥሮኮስና የበርናባስ የአክስቱ ልጅ ማርቆስ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል፤ ስለ ማርቆስ መመሪያ ደርሷችኋል፤ እንግዲህ ወደ እናንተ ሲመጣ ተቀበሉት። ኢዮስጦስ የተባለው ኢያሱም ሰላምታ ያቀርብላችኋል። ከተገረዙት መካከል ለእግዚአብሔር መንግሥት ዐብረውኝ የሚሠሩት፣ እኔንም ያጽናኑኝ እነዚህ ብቻ ናቸው፤ እነርሱም አጽናንተውናል። ከእናንተ ወገን የሆነው የክርስቶስ ኢየሱስ ባሪያ ኤጳፍራ ሰላምታ ያቀርብላችኋል፤ እርሱም ፍጹም ጠንክራችሁና ሙሉ በሙሉ ተረጋግታችሁ በእግዚአብሔር ፈቃድ ሁሉ ጸንታችሁ እንድትቆሙ ዘወትር ስለ እናንተ በጸሎት እየተጋደለ ነው። ደግሞም ስለ እናንተ እንዲሁም በሎዶቅያና በኢያራ ከተሞች ስላሉት ተግቶ እንደሚሠራ እኔ እመሰክርለታለሁ። የተወደደው ሐኪሙ ሉቃስ እንዲሁም ዴማስ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል።

ቈላስይስ 4:7-14 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

የተ​ወ​ደደ ወን​ድ​ማ​ች​ንና የታ​መነ አገ​ል​ጋይ፥ በጌታ ሥራም ተባ​ባ​ሪ​ያ​ችን የሆነ ቲኪ​ቆስ የእ​ኔን ዜና ይነ​ግ​ራ​ች​ኋል። ስለ​ዚህ ሥራ ወደ እና​ንተ የላ​ክ​ሁት ዜና​ዬን ታውቁ ዘንድ፥ ልባ​ች​ሁ​ንም ያጽ​ናና ዘንድ ነው። ወገ​ና​ችሁ ከሆ​ነው ከም​ን​ወ​ደ​ውና ከታ​መ​ነው ወን​ድ​ማ​ችን ከአ​ና​ሲ​ሞስ ጋር፥ እነ​ርሱ ሥራ​ች​ን​ንና ያለ​ን​በ​ትን ያስ​ረ​ዱ​አ​ች​ኋል። ከእኔ ጋር የተ​ማ​ረ​ከው አር​ስ​ጥ​ሮ​ኮስ፥ ወደ እና​ንተ በሚ​መጣ ጊዜ ትቀ​በ​ሉት ዘንድ ስለ እርሱ ያዘ​ዝ​ኋ​ችሁ የበ​ር​ና​ባስ የአ​ባቱ ወን​ድም ልጅ ማር​ቆ​ስም፥ ኢዮ​ስ​ጦስ የተ​ባለ ኢያ​ሱም፥ ከግ​ዙ​ራን ሰዎች ወገን የሚ​ሆኑ እነ​ዚህ ሰላም ይሏ​ች​ኋል። በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት ሥራ ረዳ​ቶች እነ​ዚህ ብቻ ናቸው፤ እነ​ር​ሱም እኔን አጽ​ና​ን​ተ​ው​ኛል። ከእ​ና​ንተ ወገን የሚ​ሆን ኤጳ​ፍ​ራ​ስም ሰላም ይላ​ች​ኋል፥ እርሱ የክ​ር​ስ​ቶስ አገ​ል​ጋይ ነው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሚ​ወ​ደው ነገር ሁሉ ምሉ​ኣ​ንና ፍጹ​ማን እን​ድ​ት​ሆኑ፥ ስለ እና​ንተ ዘወ​ትር ይጸ​ል​ያል፤ ይማ​ል​ዳ​ልም። እጅግ እን​ደ​ሚ​ወ​ዳ​ች​ሁና ስለ እና​ንተ በሎ​ዶ​ቅ​ያና በኢ​ያራ ከተማ ስላ​ሉ​ትም እን​ደ​ሚ​ቈ​ረ​ቈር እኔ ምስ​ክሩ ነኝ። ወዳ​ጃ​ችን ባለ መድ​ኃ​ኒቱ ሉቃ​ስም ሰላም ብሎ​አ​ች​ኋል፤ ዴማ​ስም ሰላም ይላ​ች​ኋል።

ቈላስይስ 4:7-14 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

የተወደደ ወንድምና የታመነ አገልጋይ በጌታም አብሮኝ ባሪያ የሆነ ቲኪቆስ ኑሮዬን ሁሉ ያስታውቃችኋል፤ ወሬያችንን እንድታውቁና ልባችሁን እንዲያጽናና፥ ከእናንተ ከሆነውና ከታመነው ከተወደደውም ወንድም ከአናሲሞስ ጋር ወደ እናንተ የምልከው ስለዚህ ምክንያት ነው፤ የዚህን ስፍራ ወሬ ሁሉ ያስታውቁአችኋል። ከተገረዙት ወገን ያሉት፥ አብሮ ከእኔ ጋር የታሰረ አርስጥሮኮስ የበርናባስም የወንድሙ ልጅ ማርቆስ ኢዮስጦስም የተባለ ኢያሱ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል፤ ስለ ማርቆስ፦ ወደ እናንተ ቢመጣ፥ ተቀበሉት የሚል ትእዛዝ ተቀበላችሁ፤ በእግዚአብሔር መንግሥት ከእኔ ጋር አብረው የሚሠሩት እነዚህ ብቻ ናቸው፥ እኔንም አጽናንተውኛል። ከእናንተ የሆነ የክርስቶስ ባሪያ ኤጳፍራ ሰላምታ ያቀርብላችኋል፤ በእግዚአብሔር ፈቃድ ሁሉ ተረድታችሁና ፍጹማን ሆናችሁ እንድትቆሙ፥ ሁልጊዜ ስለ እናንተ በጸሎቱ ይጋደላል። ስለ እናንተ በሎዶቅያም በኢያራ ከተማም ስላሉቱ እጅግ እንዲቀና እመሰክርለታለሁና። የተወደደው ባለ መድኃኒቱ ሉቃስ ዴማስም ሰላምታ ያቀርቡላችኋል።

ቈላስይስ 4:7-14 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

ቲኪቆስ ስለ እኔ ጉዳይ ሁሉንም ነገር ይነግራችኋል፤ እርሱ ተወዳጅ ወንድም፥ ታማኝ አገልጋይና በጌታ ሥራም የአገልግሎት ጓደኛዬ ነው። እርሱን ወደ እናንተ የላክሁበት ምክንያት ስለ እኛ ሁኔታ እንዲነግራችሁና ልባችሁንም እንዲያጽናና ነው። ከእርሱም ጋር የእናንተ ወገን የሆነው የታመነውና የተወደደው ወንድም ኦኔሲሞስ ወደ እናንተ ይመጣል፤ እነርሱ በዚህ ስፍራ ስላለው ነገር ሁሉ ያስታውቋችኋል። ከእኔ ጋር የታሰረው አርስጥሮኮስም ሰላምታ ያቀርብላችኋል፤ አንድ ጊዜ፥ “ወደ እናንተ በሚመጣበት ጊዜ እንድትቀበሉት” ብዬ አሳስቤአችሁ የነበረው የበርናባስ የአጐቱ ልጅ ማርቆስም ሰላምታ ያቀርብላችኋል። ኢዮስጦስ ተብሎም የሚጠራው ኢያሱ ሰላምታ ያቀርብላችኋል። ስለ እግዚአብሔር መንግሥት ከእኔ ጋር አብረው ከሚሠሩት ሰዎች መካከል የአይሁድ ወገኖች የሆኑት እነዚህ ብቻ ናቸው፤ እኔንም አጽናንተውኛል። የእናንተ ወገን የሆነው የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይ ኤጳፍራም ሰላምታ ያቀርብላችኋል፤ በመንፈሳዊ ሕይወት በማደግ ጸንታችሁ እንድትቆሙና የእግዚአብሔርንም ፈቃድ በሙሉ እንድትፈጽሙ እርሱ ስለ እናንተ በጸሎቱ ዘወትር ይጸልያል። ስለ እናንተ በሎዶቅያና በሂራፖሊስ ከተሞች ስላሉትም ሰዎች በጣም እንደሚደክም እኔ ራሴ እመሰክርለታለሁ። የተወደደው ሐኪም ሉቃስና ዴማስም ሰላምታ ያቀርቡላችኋል።

ቈላስይስ 4:7-14 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

የተወደደ ወንድምና የታመነ አገልጋይ በጌታም አብሮኝ ባርያ የሆነ ቲኪቆስ እኔ ስላለሁበት ሁኔታ ሁሉ ይነግራችኋል፤ እርሱን ወደ እናንተ የላክሁበት ዋነኛ ዓላማ እኛ በምን ዓይነት ሁኔታ ውስጥ እንደምንገኝ እንዲያሳውቃችሁና ልባችሁንም እንዲያጽናና ነው፤ ቲቂቆስም ከእናንተ ወገን ከሆነውና ከታመነው ከተወደደውም ወንድም ከኦኔሲሞስ ጋር አብሮ ይመጣል። በእዚህም ሥፍራ ስላለው ሁኔታ ሁሉ ያስታውቋችኋል። “ወደ እናንተ ቢመጣ፥ ተቀበሉት፤” የሚል ትእዛዝ የተቀበላችሁለት የበርናባስ የወንድሙ ልጅ ማርቆስ እንዳረገው እንዲሁ አብሮ ከእኔ ጋር የታሰረ አርስጥሮኮስ ሰላምታ ያቀርብላችኋል። ኢዮስጦስም የተባለ ኢያሱ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል፤ ከተገረዙትም ወገን የሆኑ፥ በእግዚአብሔር መንግሥት ከእኔ ጋር አብረው የሚሠሩት እነዚህ ብቻ ናቸው፤ እኔንም አጽናንተውኛል። ከእናንተ ወገን የሆነ የክርስቶስ ባርያ ኤጳፍራ ሰላምታ ያቀርብላችኋል፤ በእግዚአብሔር ፈቃድ ሁሉ ተረድታችሁና ፍጹማን ሆናችሁ እንድትቆሙ፥ ሁልጊዜ ስለ እናንተ በጸሎቱ ይተጋል። ስለ እናንተ በሎዶቅያም በኢያራ ከተማም ስላሉቱ እጅግ በሥራ እንደደከመ እመሰክርለታለሁና። የተወደደው ሐኪም ሉቃስ ዴማስም ሰላምታ ያቀርቡላችኋል።