በመንግሥቴ የሚኖር ሕዝብ ሁሉ የዳንኤልን አምላክ እንዲፈራና እንዲያከብር በዐዋጅ አዝዤአለሁ፤ “እርሱ ሕያውና ዘለዓለማዊ አምላክ ነው፤ መንግሥቱም የማይጠፋ ነው፤ ለመንግሥቱም ፍጻሜ የለውም፤ እርሱ ያድናል ይታደግማል፤ እርሱ በሰማይና በምድር ድንቅ ነገሮችንና ተአምራትን ያደርጋል፤ እርሱ ዳንኤልን ከአንበሶች አፍ አድኖአል።”
በመንግሥቴ ግዛት ሁሉ ያሉ ሰዎች በዳንኤል አምላክ ፊት እንዲፈሩና እንዲንቀጠቀጡ አዝዣለሁ፥ እርሱ ሕያው አምላክ ለዘላለም የሚኖር ነውና፥ መንግሥቱም የማይጠፋ ነው፥ ግዛቱም እስከ መጨረሻ ድረስ ይኖራል። ያድናል ይታደግማል፥ በሰማይና በምድርም ተአምራትንና ድንቅን ይሠራል፥ ዳንኤልንም ከአንበሶች አፍ አድኖታል።
Home
Bible
Plans
Videos