እንዲህም አለኝ፦ “ራእዩ የሚያመለክተው ስለ ዓለም መጨረሻ ስለ ሆነ በቊጣ ቀን ምን እንደሚሆን አስረዳሃለሁ። “ሁለት ቀንዶች ያሉት አውራ በግ የሜዶንንና የፋርስን ነገሥታት ያመለክታል፤ አውራው ፍየል የሚያመለክተው የግሪክን ንጉሥ ነው፤ በዐይኖቹ መካከል ያለው ትልቅ ቀንድ ደግሞ የመጀመሪያውን የግሪክ ንጉሥ ያመለክታል።
እንዲህም አለኝ፦ እነሆ፥ በመቅሠፍቱ በመጨረሻ ዘመን የሚሆነውን አስታውቅሃለሁ፥ ይህ ለተወሰነው ለፍጻሜ ዘመን ነውና። ባየኸው በአውራው በግ ላይ የነበሩ ሁለቱ ቀንዶች እነርሱ የሜዶንና የፋርስ ነገሥታት ናቸው። አውራውም ፍየል የግሪክ ንጉሥ ነው፥ በዓይኖቹም መካከል ያለው ታላቁ ቀንድ መጀመሪያው ንጉሥ ነው።
Home
Bible
Plans
Videos