ዳንኤል 8:24-25
ዳንኤል 8:24-25 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ኃይሉም ይበረታል፥ ነገር ግን በራሱ ኃይል አይደለም፥ በድንቅም ያጠፋል፥ ያደርግማል፥ ይከናወንማል፥ ኃያላንንና የቅዱሳንን ሕዝብ ያጠፋል። በመታለሉ ተንኰልን በእጁ ያከናውናል፥ በልቡም ይታበያል፥ ታምነውም የሚኖሩትን ብዙዎችን ያጠፋል፥ በአለቆቹም አለቃ ላይ ይቋቋማል፥ ያለ እጅም ይሰበራል።
Share
ዳንኤል 8 ያንብቡዳንኤል 8:24-25 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ይህም ንጉሥ እጅግ ብርቱ ይሆናል፤ ይሁን እንጂ በራሱ ኀይል አይደለም፤ እጅግ አሠቃቂ የሆነ ጥፋት ይፈጽማል፤ የሚሠራውም ሁሉ ይከናወንለታል፤ በኃያላን ሰዎችና በተቀደሱት ሕዝብ ላይ ጥፋትን ያስከትላል። እጅግም ተንኰለኛ ስለ ሆነ በማታለል ይበለጽጋል፤ ራሱንም ከሁሉ በላይ ከፍ ከፍ ያደርጋል፤ ብዙ ሰዎችን ያለ ምንም ማስጠንቀቂያ ይገድላል፤ የልዑላንን ልዑል እንኳ ይፈታተናል፤ በመጨረሻም እርሱ ራሱ ይጠፋል፤ የሚጠፋውም በሰው ኀይል አይደለም።
Share
ዳንኤል 8 ያንብቡ