ዘዳግም 30:19-20
ዘዳግም 30:19-20 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
በፊትህ ሕይወትንና ሞትን፥ በረከትንና መርገምን እንዳስቀመጥሁ እኔ ዛሬ ሰማይንና ምድርን በአንተ ላይ አስመሰክራለሁ፤ እንግዲህ አንተና ዘርህ በሕይወት ትኖሩ ዘንድ ሕይወትን ምረጥ፤ እግዚአብሔርም ለአባቶችህ ለአብርሃምና ለይስሐቅ ለያዕቆብም እንዲሰጣቸው በማለላቸው በምድሪቱ ትቀመጥ ዘንድ፥ እርሱ ሕይወትህ፥ የዘመንህም ርዝመት ነውና አምላክህን እግዚአብሔርን ውደደው፤ ቃሉን ስማው፤ አጥናውም።”
ዘዳግም 30:19-20 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
በፊታችሁ ሕይወትንና ሞትን በረከትንና መርገምን እንዳስቀመጥሁ እኔ ዛሬ ሰማይንና ምድርን በአንተ ላይ አስመሰክራለሁ፤ እንግዲህ አንተና ዘርህ በሕይወት ትኖሩ ዘንድ ሕይወትን ምረጥ፤ እግዚአብሔርም ለአባቶችህ ለአብርሃምና ለይስሐቅ ለያዕቆብም እንዲሰጣቸው በማለላቸው በምድሪቱ ትቀመጥ ዘንድ፥ እርሱ ሕይወትህ የዘመንህም ርዝመት ነውና አምላክህን እግዚአብሔርን ትወድደው ትጠባበቀውም ቃሉንም ትሰማ ዘንድ ምረጥ።
ዘዳግም 30:19-20 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
እነሆ፥ እኔ በሕይወትና በሞት መካከል፥ በእግዚአብሔር በረከትና መርገም መካከል ምርጫ እሰጣችኋለሁ፤ በምታደርጉትም ምርጫ ሰማይንና ምድርን በአንተ ላይ ምስክር አድርጌ እጠራለሁ፤ ስለዚህም እናንተና ዘሮቻችሁ በሕይወት ትኖሩ ዘንድ ሕይወትን ምረጡ። አምላክህን እግዚአብሔርን ውደድ፤ ለእርሱም ታዛዥ ሁን፤ በእርሱም እመን፤ ይህም ለአንተ ሕይወት ከመሆኑም በላይ ለቀድሞ አባቶችህ ለአብርሃም፥ ለይስሐቅና ለያዕቆብ በመሐላ ቃል በገባላቸው መሠረት ገብተህ በምትኖርባት ምድር ለረጅም ዘመን ትኖራለህ።”