ዘፍጥረት 37:31-34
ዘፍጥረት 37:31-34 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
የዮሴፍንም ቀሚስ ወሰዱ፤ የፍየልም ጠቦት አርደው ቀሚሱን በደም ነከሩት። ብዙ ኅብር ያለበትን ቀሚሱንም ላኩ፤ ወደ አባታቸውም አገቡት፤ እንዲህም አሉት፥ “ይህን ልብስ አገኘን፤ ይህ የልጅህ ልብስ እንደ ሆነ ወይም እንዳልሆነ እስኪ እየው?” እርሱም ዐውቆ፥ “የልጄ ቀሚስ ነው፤ ክፉ አውሬ በልቶታል፤ ዮሴፍን ቦጫጭቆታል” አለ። ያዕቆብም ልብሱን ቀደደ፤ በወገቡም ማቅ ታጥቆ ለልጁ ብዙ ቀን አለቀሰ።
ዘፍጥረት 37:31-34 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ከዚያም የዮሴፍን እጀ ጠባብ ወሰዱ፤ አንድ ፍየልም ዐርደው እጀ ጠባቡን በደሙ ነከሩት። በኅብረ ቀለማት ያጌጠችውን እጀ ጠባብ ወደ አባታቸው ወስደው፣ “ይህን ወድቆ አገኘነው፤ የልጅህ እጀ ጠባብ መሆን አለመሆኑን እስኪ እየው” አሉት። እርሱም ልብሱን ዐውቆት፣ “ይህማ የልጄ እጀ ጠባብ ነው! ክፉ አውሬ በልቶታል፤ በርግጥም ዮሴፍ ተቦጫጭቋል” አለ። ከዚህ በኋላ ያዕቆብ ልብሱን ቀደደ፤ ማቅም ለብሶ ስለ ልጁ ብዙ ቀን አለቀሰ፤
ዘፍጥረት 37:31-34 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
የዮሴፍንም ቀሚስ ወሰዱ የፍየል አውራም አርደው ቀሚሱን በደም ነከሩት። ብዙ ኅብር ያለበት ቀሚሱንም ላኩ፥ ወደ አባታቸውም አገቡት እንዲህም አሉት፦ ይህንን አገኘነ ይህ የልጅህ ልብስ እንደ ሆነ ወይም እንዳልሆነ እስኪ እየው። እርሱም አውቆ፦ የልጄ ቀሚስ ነውም ክፋ አውሬ በልቶታል ዮሴፍ በእርግጥ ተበጫጭቋል አለ ያዕቆብም ልብሱን ቀደደ በወገቡም ማቅ ታጥቆ ለልጁ ብዙ ቀን አለቀሰ።
ዘፍጥረት 37:31-34 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ከዚህ በኋላ አንድ ፍየል ዐረዱና የዮሴፍን ልብስ በደም ነከሩት። ብዙ ኅብር ያለበትንም ልብሱን ወደ አባታቸው ወስደው “እነሆ፥ ይህን አገኘን የልጅህ ልብስ እንደ ሆነ ወይም እንዳልሆነ እይ” አሉት። እርሱም የልጁ ልብስ መሆኑን ተረድቶ “በእርግጥ የእርሱ ልብስ ነው! አንድ ክፉ አውሬ ገድሎታል፤ ልጄን ዮሴፍን አውሬ ቦጫጭቆ በልቶታል!” አለ። ከዚህ በኋላ ልብሱን በሐዘን ቀደደ፤ ማቅ በወገቡ ታጥቆ ለልጁ ብዙ ቀኖች አለቀሰ።