ዘፍጥረት 46:15 - ሁሉንም ስሪቶች ያወዳድሩ

ዘፍጥረት 46:15 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

እነዚህ ወንዶች ልጆች ያዕቆብ በሰሜን ምዕራብ መስጴጦምያ ሳለ፣ ልያ የወለደችለት ናቸው። ሴቷን ዲናን ጨምሮ፣ የወንዶችና የሴቶች ልጆቹ ቍጥር ሠላሳ ሦስት ነው።

ዘፍጥረት 46:15 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

እነዚህ ወንዶች ልጆችና ሴቷም ልጅ ዲና በመስጴጦምያ ሳሉ ልያ ለያዕቆብ የወለደችለት ናቸው። ያዕቆብ ከልያ ያፈራቸው ልጆችና የልጅ ልጆች ሠላሳ ሦስት ናቸው።

ዘፍጥረት 46:15 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

ልያ በመ​ስ​ጴ​ጦ​ምያ በሶ​ርያ ለያ​ዕ​ቆብ የወ​ለ​ደ​ቻ​ቸው ልጆ​ችና ሴቲቱ ልጅዋ ዲና እነ​ዚህ ናቸው፤ ወን​ዶ​ችም ሴቶ​ችም ልጆ​ችዋ ሁሉ ሠላሳ አራት ነፍስ ናቸው።

ዘፍጥረት 46:15 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

ልያ በመስዼጦምያ በሶርያ ለያዕቆብ የወለደቻቸው ልጆችና ሴቲቱ ልጅዋ ዲና እነዚህ ናቸው ወንዶችም ሴቶችም ልጆችዋ ዲና እነዚን ናቸው ወንዶችም ሴቶችም ልጆችዋ ሁሉ ሠላሳ ሦስት ነፍስ ናቸው።

ዘፍጥረት 46:15 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

ልያ በፓዳን-ኣሪም በሶርያ ለያዕቆብ የወለደቻቸው ልጆችና፥ ሴቲቱ ልጇ ዲና እነዚህ ናቸው፥ ወንዶችም ሴቶችም ልጆችዋ ሁሉ ሠላሳ ሦስት ናቸው።