ኢሳይያስ 35:3-4
ኢሳይያስ 35:3-4 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
የደከሙትን እጆች አበርቱ፤ የላሉትንም ጕልበቶች አጽኑ፤ የሚፈራ ልብ ላላቸው እንዲህ በሉ፤ “በርቱ፤ አትፍሩ፤ አምላካችሁ ይመጣል፤ ሊበቀል ይመጣል፤ እርሱም ብድራቱን ይዞ፣ ሊያድናችሁ ይመጣል።”
Share
ኢሳይያስ 35 ያንብቡኢሳይያስ 35:3-4 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ደካሞች እጆችና አንካሶች ጕልበቶች፥ ጽኑ። እናንተ አእምሮ የሌላችሁ፥ ልቡናችሁን አረጋጉ፤ ጽኑ፤ አትፍሩ፤ እነሆ፥ አምላካችን ፍርድን ይመልሳል፤ ይበቀላልም፤ እርሱም መጥቶ ያድነናል።
Share
ኢሳይያስ 35 ያንብቡኢሳይያስ 35:3-4 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
የደከሙትን እጆች አበርቱ፥ የላሉትንም ጕልበቶች አጽኑ። ፈሪ ልብ ላላቸው፦ እነሆ፥ አምላካችሁ በበቀል በእግዚአብሔርም ብድራት ይመጣልና፥ መጥቶም ያድናችኋልና በርቱ፥ አትፍሩ በሉአቸው።
Share
ኢሳይያስ 35 ያንብቡ