ኢሳይያስ 40:6-7
ኢሳይያስ 40:6-7 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
አንድ ድምፅ “የዐዋጅ ቃል ተናገር!” እያለ ይጮኻል። እኔም “ምን ብዬ ላውጅ!” ስል ጠየቅሁ። ያም ድምፅ “እንዲህ ብለህ ዐውጅ” አለኝ፦ “ሰው ሁሉ እንደ ሣር ነው፤ ክብሩም ሁሉ እንደ ሜዳ አበባ ነው፤ የእግዚአብሔር ነፋስ በሚነፍስበት ጊዜ፥ ሣሩ እንደሚደርቅና አበባውም እንደሚረግፍ ሰውም እንዲሁ ረጋፊ ነው።
Share
ኢሳይያስ 40 ያንብቡኢሳይያስ 40:6-7 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
“ጩኽ” የሚል ሰው ቃል፤ “ምን ብዬ ልጩኽ?” አልሁ። “ሥጋ ለባሽ ሁሉ ሣር ነው፤ የሰውም ክብሩ ሁሉ እንደ ሣር አበባ ነው። የእግዚአብሔር እስትንፋስ ይነፍስበታልና ሣሩ ይደርቃል፤ አበባውም ይረግፋል፤ በእውነት ሕዝቡ ሣር ነው።
Share
ኢሳይያስ 40 ያንብቡኢሳይያስ 40:6-7 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ድምፅም፣ “ጩኽ” አለኝ፤ እኔም፣ “ምን ብዬ ልጩኽ?” አልሁ። “ሰው ሁሉ እንደ ሣር ነው፤ ክብሩም ሁሉ እንደ ሜዳ አበባ ነው። ሣሩ ይደርቃል፤ አበባውም ይረግፋል፤ የእግዚአብሔር እስትንፋስ ነፍሶበታልና፤ ሕዝቡ በርግጥ ሣር ነው።
Share
ኢሳይያስ 40 ያንብቡ