ኢሳይያስ 46:10-11
ኢሳይያስ 46:10-11 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
በመጨረሻ የሚሆነውን ነገር ከመጀመሪያው ጀምሬ ተናግሬአለሁ፤ ወደፊት ምን እንደሚሆን ከጥንት ጀምሬ ገልጬአለሁ፤ ዓላማዬ የጸና ይሆናል፤ የምፈቅደውንም አደርጋለሁ። ከወደ ምሥራቅ እንደ ነጣቂ ጭልፊት ያለውን እጠራለሁ፤ እርሱም ዓላማዬን የሚፈጽም፥ ከሩቅ አገር የሚመጣ ሰው ነው፤ የተናገርኩትን አደርጋለሁ፤ ያቀድኩትንም እፈጽማለሁ።
Share
ኢሳይያስ 46 ያንብቡኢሳይያስ 46:10-11 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
በመጀመሪያ መጨረሻውን፥ ከጥንትም ያልተደረገውን እናገራለሁ፤ ምክሬ ትጸናለች፤ የመከርሁትንም ሁሉ አደርጋለሁ እላለሁ። ከምሥራቅና ከሩቅ ሀገር ስለ መከርሁት ምክር ዎፍን እጠራለሁ፤ ተናገርሁ፤ አመጣሁም፤ ፈጠርሁ፤ አደረግሁም፤ አመጣሁት፤ መንገዱንም አቀናሁለት።
Share
ኢሳይያስ 46 ያንብቡኢሳይያስ 46:10-11 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
የመጨረሻውን ከመጀመሪያው፣ ገና የሚመጣውንም ከጥንቱ ተናግሬአለሁ፤ ‘ምክሬ የጸና ነው፤ ደስ የሚያሠኘኝንም ሁሉ አደርጋለሁ’ እላለሁ። ከምሥራቅ ነጣቂ አሞራ፣ ከሩቅ ምድር ዐላማዬን የሚፈጽም ሰው እጠራለሁ። የተናገርሁትን አደርጋለሁ፤ ያቀድሁትን እፈጽማለሁ።
Share
ኢሳይያስ 46 ያንብቡ