ኢሳይያስ 48:17-18
ኢሳይያስ 48:17-18 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
እናንተን የሚያድን የእስራኤል ቅዱስ እግዚአብሔር አምላክ እንዲህ ይላል፤ “የሚጠቅምህን ሁሉ የማስተምርህና ልትሄድበት የሚገባህን መንገድ የምመራህ እግዚአብሔር አምላክህ እኔ ነኝ። “ትእዛዞቼን በጥንቃቄ ሰምታችሁ ቢሆንማ ኖሮ፥ በረከታችሁ እንደማይደርቅ የወንዝ ውሃ፥ ጽድቃችሁም እንደ ባሕር ሞገድ በብዛት በመጣላችሁ ነበር!
Share
ኢሳይያስ 48 ያንብቡኢሳይያስ 48:17-18 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ታዳጊህ፥ የእስራኤል ቅዱስ፥ እንዲህ ይላል፥ “እኔ የሚረባህን ነገር የማስተምርህ የምትሄድባትንም መንገድ እንዴት እንደምታገኝ የምመራህ አምላክህ እግዚአብሔር ነኝ። ትእዛዜን ብትሰማ ኖሮ፥ ሰላምህ እንደ ወንዝ ጽድቅህም እንደ ባሕር ሞገድ በሆነ ነበር፤
Share
ኢሳይያስ 48 ያንብቡኢሳይያስ 48:17-18 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
የተቤዠህ፣ የእስራኤል ቅዱስ፣ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “እኔ እግዚአብሔር አምላክህ፣ የሚበጅህ ምን እንደ ሆነ የማስተምርህ፣ መሄድ በሚገባህ መንገድ የምመራህ ነኝ። ትእዛዜን ሰምተህ ብቻ ቢሆን ኖሮ፣ ሰላምህ እንደ ወንዝ፣ ጽድቅህም እንደ ባሕር ሞገድ በሆነ ነበር።
Share
ኢሳይያስ 48 ያንብቡኢሳይያስ 48:17-18 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ታዳጊህ፥ የእስራኤል ቅዱስ፥ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እኔ የሚረባህን ነገር የማስተምርህ በምትሄድባትም መንገድ የሚመራህ አምላክህ እግዚአብሔር ነኝ። ትእዛዜን ብትሰማ ኖሮ፥ ሰላምህ እንደ ወንዝ ጽድቅህም እንደ ባሕር ሞገድ በሆነ ነበር፥
Share
ኢሳይያስ 48 ያንብቡ