ኢሳይያስ 51:3
ኢሳይያስ 51:3 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ደስ አሰኝሻለሁ፤ ባድማሽንም ሁሉ ደስ አሰኛለሁ፤ ምድረ በዳሽንም እንደ ዔድን፥ በረሃዎችሽንም እንደ እግዚአብሔር ገነት አደርጋለሁ። ደስታና ተድላ እምነትና የዝማሬ ድምፅ በውስጧ ይገኝባታል።
ኢሳይያስ 51:3 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
እግዚአብሔር ጽዮንን በርግጥ ያጽናናታል፤ ፍርስራሾቿንም በርኅራኄ ይመለከታል፤ ምድረ በዳዋን እንደ ዔድን፣ በረሓዋንም እንደ እግዚአብሔር ተክል ቦታ ያደርጋል፤ ተድላና ደስታ፣ ምስጋናና የዝማሬ ድምፅ በርሷ ይገኛሉ።
ኢሳይያስ 51:3 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
እግዚአብሔርም ጽዮንን ያጽናናል፥ በእርስዋም ባድማ የሆነውን ሁሉ ያጽናናል፥ ምድረ በዳዋንም እንደ ዔድን በረሀዋንም እንደ እግዚአብሔር ገነት ያደርጋል፥ ደስታና ተድላ ምስጋናና የዝማሬ ድምፅ ይገኝበታል።