ኢሳይያስ 54:8
ኢሳይያስ 54:8 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
በጥቂት ቍጣ ፊቴን ከአንቺ ሰወርሁ፤ በዘለዓለም ቸርነት ይቅር እልሻለሁ፥ ይላል ታዳጊሽ እግዚአብሔር።
ኢሳይያስ 54:8 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ለጥቂት ጊዜ እጅግ ስለ ተቈጣሁ፣ ፊቴን ከአንቺ ሰወርሁ፤ ነገር ግን በዘላለማዊ ቸርነቴ፣ እራራልሻለሁ” ይላል ታዳጊሽ እግዚአብሔር።
ኢሳይያስ 54:8 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
በጥቂት ቍጣ ለቅጽበተ ዓይን ፊቴን ከአንቺ ሰወርሁ፥ በዘላለምም ቸርነት እምርሻለሁ፥ ይላል ታዳጊሽ እግዚአብሔር።