ኤርምያስ 15:19
ኤርምያስ 15:19 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ብትመለስ እመልስሃለሁ፤ በፊቴም ትቆማለህ፤ የከበረውንም ከተዋረደው ብትለይ እንደ አፌ ትሆናለህ፤ እነርሱ ወደ አንተ ይመለሳሉ፤ አንተ ግን ወደ እነርሱ አትመለስም።
ኤርምያስ 15:19 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ብትመለስ፣ መልሼ አቆምሃለሁ፤ ታገለግለኛለህም፤ የከበረውን ከማይረባው ለይተህ ብትናገር፣ አፍ ትሆነኛለህ፤ እነርሱ ወደ አንተ ይመለሳሉ እንጂ፣ አንተ ወደ እነርሱ አትመለስም፤
ኤርምያስ 15:19 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ብትመለስ እመልስሃለሁ በፊቴም ትቆማለህ፥ የከበረውንም ከተዋረደው ብትለይ እንደ አፌ ትሆናለህ፥ እነርሱ ወደ አንተ ይመለሳሉ፥ አንተ ግን ወደ እነርሱ አትመለስም።